እንዴት እንደዚህ ያለ ውርደት ተዋርደን ምላሽ ሳንሰጥ እናልፋለን? በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው።

Freedom4Ethiopian

በዘሪሁን ሙሉጌታ
 
በመጪው እሁድ በታላቅ ድምቀት በሚካሄደውና በአፍሪካ በግዙፍነቱ ቀዳሚ በሆነው ‘‘ታላቁ ሩጫ’’ ላይ የሚሮጡ ተሳታፊዎች በሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጉዳት በሐዘን ለመግለፅ ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበውን ጥሪ የ‘‘ታላቁ ሩጫ’’ አስተባባሪዎች ተቃወሙ።
የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባላት በሳዑዲ አረቢያ የተፈናቀሉ ዜጎች ላይ የደረሰውን ግፍና በደል ለዓለም አቀፍ ህብረተሰብና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማስገንዘብ በሩጫው የሚካፈሉ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን በማድረግ ሐዘናቸውን እንዲገልፁ ሲል ወስኗል። የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች በጉዳዩ ላይ እንዲተባበሩና አጋርነታቸውን እንዲገልፁ ለማድረግ በደብዳቤ ጥያቄውም እንደሚያቀርብ የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት አስታውቋል።
የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ግን የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አንደግፈውም ሲሉ ጥሪውን ተቃውመዋል። ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት ዳግማዊት አማረ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ‘‘ፕሮግራሙ የስፖርት ዝግጅት ነው፤ ዓላማውም የተለየ ነው፤ ሕብረተሰቡን ማቀራረብና ሀገሪቱን በበጎ አይን ማስተዋወቅ ነው። ስፖርት ዋናው ተልዕኮው ሰላም ነው። በዝግጅቱም ላይ የራሳችን ዓላማ አለን። ሁሉም ሰው ለዚህ አላማ እንዲሮጥ ነው የምንፈልገው። ከዚህ ቀደም በተባበሩት መንግስታት የተቀየሱ ስምንቱ የልማት ግቦች እንዲሳኩ ባለፉት አራት አመታት ያንን ስናስተጋባ ቆይተናል። በዘንድሮ አመትም ‘‘ለተሻለች…

View original post 243 more words