ባለትዳሮች ሆይ …. አትጨቅጭቁን!

«ዘውድአለም ታደሰ»

የተከበራችሁ የፌስቡክ ጓደኞቼ ፣ መካሪዎቼ ፣ ዘካሪዎቼ ፣ አድናቂዎቼ (እዚች ጋር ፈገግ እንላለን) ፣ በውጭም በሃገር ውስጥም ያላችሁ፣ ወይም የሌላችሁ (ምን ነካኝ ዛሬ?) …. ሃብታሞች ፣ ድሆች ፣ ወይም እንደኔ ከድህነት ወለል በታች ያላችሁ ችስታዎች (አረ በቃህ ዘውድአለም) … አጫጭሮች ፣ ረጃጅሞች ፣ ወንዶች ፣ ሴቶች ፣ (እጃችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ ልበል እንዴ እንደዛ ዘፋኝ?) … አዛውንቶች ፣ ወጣቶች እንዲሁም ህፃናት …. ባጠቃላይ ሁላችሁም እንዴት ዋላችሁ? (እንዴት ዋላችሁ ለማለት ይሄ ሁሉ ጭቅጭቅ?) ሁፍፍፍ!

እኔ ምለው ጓዶች …የኬኒያ ነገር ምንም አልዋጥ ብሎኛል! ቆይ አፍሪካውያን ላይ ግን የሆነ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ምናምን የሚሉት ነገር አያምርም ኣ? ሃይሊሻኮ እውነቷን ነው። አስ አፍሪካን ሲቲዝን ዴሞክራሲ ኢዝ ቅንጦት!
እኛ ላይ ሚያምረው ውጤቱ በተጠራጠረበት ክልል ላይ መንግስት ኮሮጆውን ሰርቆ በአዲስ ሲተካው … ተቃዋሚዎች ወደውና ፈቅደው ከተወዳደሩ በኋላ “ተሸንፋችኋል” ሲባሉ “ምርጫ ቦርዱ ገለልተኛ አይደለም” ብለው ሲቀውጡት … ምስኪኑ ህዝብም ሆ ብሎ በቁጣ ሰልፍ ሲወጣ የመንግስት ታጣቂዎች ህዝቡን በጥይት ገደል ገደል አድርገው ተመጣጣኝ እርምጃ ሲወስዱ ……. ምናምን ነው ሚያምርብን! ታዲያ ኬኒያ ምናባቷ ሆና ነው በአፍሪካ ተሰምቶ የማያውቅ ታሪክ የሰራችው? ምርጫ መጭበርበር ብርቅ ነው እንዴ? ምነው ቀበጡ? ምነው ሽንታችን ፔፕሲ ኮላ ነው አሉ! የጎረቤት ሐገር ህዝብ ይቀናል ምናምን አይባልም እንዴ? ሼም ኦን ዩ ኬንያ!!

(የኬንያን መጨረሻ ያሳምረው እያልኩ አንድ ግርም ያለኝን ነገር ነግሪያችሁ ልንካው …)

ቆይ እኔ ምለው … «ሰው ሁሉ ያግባ!» የሚል አዋጅ ፀደቀ እንዴ ባገሩ? እኛኮ ዜና አንሰማም ከፀደቀ ንገሩኝ። እንዴዬዬ …. ሰው ሁሉ በትዳር ተቧድኖ አለቀኮ!
በተለይ ደግሞ መጨረሻው ዘመን ላይ መሆናችንን ያወቅሁት ጓደኛዬ ሰብስቤ ያገባ ቀን ነው 🙂 ሰብስቤኮ ትዳር ውስጥ ግባ ከሚባል ቅልጥ ያለ ጦርነት መሃል ቢጥሉት የሚመርጥ ሰው ነበር! ለነገሩ ላግባ ቢል ራሱ ማንን እንደሚያገባ ይቸገር ነበር። ጠኋት አንዷን ጠይም ዘለግ ያለች አቅፎ ይታያል ፣ ከሰአት ሌላዋን ይዞ ባጠገባችን ሽው ይላል ፣ እንደገና ነገ ሌላዋን ፣ ተነጎዲያ ሌላዋን … ስምን መላክ ያወጣዋል አሉ! እውነትም ሰብስቤ!

አሁን ግን ባለትዳር ሆኗል! ይሁን የራሱ ጉዳይ! አላስቀምጥ ያለኝ ምክሩ ነው!
«እኔ ምልህ … » ብሎ ሲጀምር ገና «በመድሃኒአለም ይዠሃለሁ እንዳትመክረኝ» እለዋለሁ!
«ልመክርህ አይደለም» ይልና ምክሩን ይጀምራል ….

«ዜድ ሁሌ ከምትንዘላዘል ለምን አንዷን አግብተህ ቁጭ አትልም?» ይለኛል።
«የታባህ ስንዘላዘል አየኸኝ?» እለዋለሁ ተኮሳትሬ።
«ሂሂ እሱን እንኳ ተወው! ጠቢቡ ሰለሞን የሚበልጥህ በእድሜ ብቻ አይደል እንዴ? ሂሂ» እያለ ያገጣል! ዝም እለዋለሁ ።
«ዜድ ከኔ ለምን አትማርም? ካገባሁ ወዲህ እንዴት ብር ራሱ መቆጠብ እንደጀመርኩ መቼም አይተሃል!»
«ታዲያ ለምን በየቀኑ እየመጣህ አንዴ ለቤት ኪራይ አንዴ ለዳይፐር እያልክ ትበደረኛለህ?»
«ያው ሰው ሁኖ ማይበደር የለም እሱማ!»
«ሂሂ»
«ሱስም ቢሆን አቁሚያለሁ። ካገባሁ በኋላ ስጠጣ አይተኸኝ ታውቃለህ?»
«በየቀኑ ነዋ»
«እሱማ ሰው ሆኖ ማይጠጣ የለም። ግን ከበፊቱ ጋር ስነፃፀር መጠጥ አቁሚያለሁ ነው ሚባለው» አለኝ ፍጥጥ ብሎ።
«አንተ የራስህ ጉዳይ እኔን ግን አትምከረኝ» እለዋለሁ።
«ቆይ ልጅ ወልደህ አይንህን በአይንህ ማየት አትፈልግም?»
«አልፈልግም»
«እኔን እየኝ እስቲ ከወለድኩ በኋላ …. » ብሎ ሊቀጥል ሲል
«ሰውዬ መች ወለድክና?» ብዬ ሳቋርጠው …
«ያው ተረግዞ የለ መወለዱ የት ይቀራል?» ሃሃ ብሎ ምክሩን ይቀጥላል!

አረ ባለትዳሮች ስለፈጠራችሁ ተዉን! በቃ ተዉና! የአልቤርጎ ወጪ አማሯችሁ እንደተጋባችሁ አናውቅም እንዴ? የቤት ኪራይ ሼር ለማድረግ እንደተቧደናችሁ አናውቅም እንዴ? (አንዳንዶቻችሁ እንደውም ባለትዳር ሳይሆን ሩምሜት ነው መባል ያለባችሁ)
እንተዋወቅ የለም እንዴ ጎበዝ? የምን ጭቅጭቅ ነው? በቃ አናገባም ካልን አናገባም ነው ተዉን! በተለይ አዲስ ባለትዳሮች ብታርፉ ይሻላችኋል!

«ጀማሪ ጿሚ ደጄ ላይ በግ አትሰሩ ይላል» አሉ አበው!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.