የ2009 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማት እጩዎች የሚከተሉት ናቸው

መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ

1. ዶ/ር መስፍን አርአያ (ለብዙ ዓመታት የዐማኑኤል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ የአእምሮ ሕክምና ባለሞያ)
2. አቶ ገመቹ ዲቢሶ(ዋናው ኦዲተር)
3. አቶ ማቴዎስ አስፋው(የአዲስ አበባ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር)

ሚዲያና ጋዜጠኛነት

 1. እሸቴ አሰፋ (የሸገር ጋዜጠኛ)
 2. ንጉሤ አክሊሉ (ለብዙ ዓመታት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ያገለገለና በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካ ድምጽ ጋዜጠኛ)
 3. ሸገር ሬዲዮ ጣቢያ

ማኅበራዊ ጥናት

 1. ኤመሪተስ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ (የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ፣ የታሪክ መምህርና የታሪክ መጻሕፍት ደራሲ)
 2. ዶ/ር የራስ ወርቅ አድማሴ (በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ(አአዩ) የነገረ ማኅበረሰብ ተመራማሪ)
 3. ዶ/ር ካሣሁን ብርሃኑ (በአአዩ የፖለቲካ ሳይንስ

ተባባሪ ፕሮፌሰር)

ለኢትዮጵያ መልካም የሠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች

 1. ቦብ ጌልዶፍ (በ1977 ድርቅ ወቅት ዓለም ዐቀፍ የሙዚቃ ባለሞያዎችን አስተባብሮ ለኢትዮጵያ ርዳታ የሰበሰበ)
 2. ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን(የፊስቱላ ሆስፒታል መሥራች)
 3. ፕሮፌሰር ጃኮብ ሽናይደር (በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚያገለግሉ የስዊዘርላንድ ሐኪም)

ቅርስ፣ ባሕልና ቱሪዝም

 1. ጉዞ አድዋ (ወጣቱ የአድዋን ታሪክ እንዲያስብና እንዲያከብር በማድረግ)
 2. አቶ ገብረ ኢየሱስ ኃይለ ማርያም (የጉራጌ አካባቢ ቅርሶችንና ባህልን በማጥናት፣ በመጠበቅና በማሰባሰብ)
 3. የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቤተ መዛግብት ማዕከል (ባለፉት መንግሥታት ዘመን የነበሩትን የየመሥሪያ ቤቶችን ታሪካዊ መዛግብት በማሰባሰብ፣ በማጥናትና ለጥናትና ምርምር ምቹ በማድረግ)

ሳይንስ

 1. ዶ/ር ቦጋለ ሰሎሞን (የካንሰር ስፔሻሊስት)
 2. ሎሬት ዶክተር ለገሠ ወልደ ዮሐንስ(ከዶክተር አክሊሉ ለማ ጋር በመሆን የብልሐርዚያን መድኃኒት ያገኙ)
 3. ኤመሪተስ ፕሮፌሰር ንጉሤ ተበጀ(በአአዩ፣ ተባባሪ ፕሮፌሰር)

ኪነ ጥበብ(በቴአትር ዘርፍ)

 1. ተስፋዬ ገሠሠ(ታዋቂ የቴአትር ባለሞያና መምህር)
 2. ጌትነት እንየው (ገጣሚ፣ ተዋናይ፣ ጸሐፌ ተውኔትና አዘጋጅ)
 3. ዓለማየሁ ታደሰ(ተዋናይ፣ አዘጋጅና የቴአትር መምህር)

ንግድና የሥራ ፈጠራ

 1. ኢንጅነር ጸደቀ ይሁኔ (የፊሊን ስቶን ባለቤት)
 2. አቶ ሰሎሞን ሙሉጌታ (የእሹሩሩ የሥልጠና ማዕከል ባለቤት)
 3. ሸዋ ዳቦ (ለ60 ዓመታት በዱቄትና ዳቦ ዘርፍ የሠራ ተቋም)

መምህርነት

 1. መ/ር ፈቃደ ደጀኔ (ከ1970 ዓም ጀምሮ በመምህርነት በመርሐ ቤቴና አርሲ ያስተማሩ፤ በገጠር ትምህርት ቤት ያሠሩ፣ ልጆችን እየረዱ የሚያስተምሩ)
 2. መ/ር ሰሎሞን ጸደቀ (በወሎ ቦረና፣ ጋሞጎፋ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ወለጋ፣ ጉራጌ ዞን ከ1973 ዓም ጀምሮ የሠሩ፤ በገጠር ትምህርት ቤቶችን ያሠሩ፣ ለገጠሩ ሕዝብ የልማት ተቋማትን ያስገነቡ፣ ትምህርታቸው የሚያቋርጡ ተማሪዎች የሚረዱበትን መንገድ የፈጠሩ)
 3. አቶ ማሞ ከበደ ሸንቁጥ (የታወቁ የትምህርት ባለሞያ፣ በተለይም ደግሞ በጎልማሶች ትምህርት ላይ ለውጥ ያመጡ)

በጎ አድራጎት

 1. መቅደስ ዘለለው (የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ድርጅት(IFSO) መሥራችና መሪ)
 2. ዳዊት ኃይሉ( የውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ባለቤት፤ ለብዙ ችግረኛ ሕሙማን በነጻና በሚችሉት ክፍያ አገልግሎት የሚሰጥ)
 3. ሰሎሞን ይልማ (በደብረ ዘይት ከተማ ችግረኞችን በመርዳት የሚታወቅ ወጣት)

ከዳንኤል ክብረት

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.