በኦሮሚያ ክልል 6700 ሰዎች ሃሰተኛ ሠነዶች ይዘው ተገኙ

ቁጥራቸው 6700 የሚሆን የኦሮሚያ ክልል የህዝብ ሰራተኞች የመንጃ ፈቃዶች እና የብቃት መማረጋገጫ ሰርቲፊኬትን (ሲኦሲ) ጨምሮ ሃሰተኛ የስራ እና የትምህርት ሠነዶችን ይዘው ተገኝተዋል። የኦሮሚያ ክልል የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀይል ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሰራተኞቹ የአመራር ስፍራን ጨምሮ በተለያዩ መደቦች ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል።

እንደ ሀላፊው ገለፃ ግማሽ ሚሊዮን ከሚሆነው የመንግስት ስራ ላይ የተሰማራ ሰው አንፃር አሃዙ አነስተኛ ነው ብለዋል። ነገር ግን በምስክሮች እና በመርማሪዎች እገዛ በሃሰተኛ ሠነዶች የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ቁጥር መጋለጥ ሊጨምር እንደሚችል አሳውቀዋል።

ዶ/ር ቢቂላ አክለውም ከጊዜ ጊዜ እያደገ የመጣው የሃሰተኛ ሠነዶች ጉዳይ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ብልሹነት ቢሮውን ለምርመራ እንደዳረገው ይናገራሉ።

ቢሮው እጃቸው ላይ ሃሰተኛ ሠነዶች ይዘው የሚገኙ ሰዎች ከሰኔ እስከ ሓምሌ 2009 ዓ.ም. ባለው ጊዜ በራሳቸው ፈቃድ እንዲያስረክቡ የእፎይታ ጊዜ ሰጥቶ እንደነበር ሃላፊው አስታውሰዋል። ይህንን ተከትሎም ሃሰተኛ ሠነዶች እንዳላቸው ያሳወቁ ግለሰቦች ባላቸው እውነተኛ ሠነዶች መሠረት ስራ ገበታቸው ላይ እንደተመደቡም ሃላፊው አስታውቀዋል።

ነገር ግን በተሰጣቸው ጊዜ ሃሰተኛ ሠነዶችን ማስረከብ ያልቻሉ ሰዎች ምርመራ ተደርጎባቸው ከስራቸው እንዲሰናበቱ መደረጉም ታውቋል። ባልተገባ መንገድ ሲቀበሉ የነበረውን ደሞዝ እና ጥቅማጥቅምም እንዲመልሱ እንደሚደረግ ዶ/ር ቢቂላ አስረግጠዋል።

ሃሰተኛ ሠነዶች ይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችን የእምነት ክህደት ቃልን ከመሰብሰብ ጀምሮ ያደረጓቸው የስልክ ልውውጦች እንደ መረጃ እንደሚቀርብባቸው እና ምርመራው እስከ መጪው መስከረም 22. 2010 ዓ.ም. ድረስ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ቢሮው አዲስ የተቀላቀሉ የመንግስት ሰራተኞችም ላይ የሰነድ ማጣራት ምርመራ ወደፊት እንደሚካሄድባቸው አስታውቋል።


 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.