በአበበ ቢቂላ ስም የተሰየመው የሽልማት መርሃ ግብር

ይህ መርሃ ግብር የጀመረው ለጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ ማስታወሻነትና ስራዎቹን ለመዘከር ነው። ስለቢቂላ ለኢትዮጵያዊ ማስረዳት ለቀባሪው ማርዳት ይሆናል።

Ethiopia and the Red Sea
Ethiopia and the Red Sea

የቢቂላ ሽልማት መስራቾች አላማ

  • ወጣቶችን ማበረታታት
  • ወጣቶች ከፍ ላለ አላማ እንዲሮጡ
  • ወጣቶች ውቴታማ እንዲሆኑ

ለዚህም ነው በተሰማሩበት የስራ መስክ ታላቅ አስተዋፆኦ ያስመዘገቡ ኢትዮጵያውያንን በየአመቱ የሚሸልመው።

ለሽልማቱ የተመረጡት ዘርፎች:

  • በትምህርቱ
  • በስፖርት
  • በማህበራዊ ስራዎች
  • በስነ-ስዕል
  • በስነ-ፅሁፍ
  • ሳይንስና ቴክኖሎጂ
  • ቢዝነስ እና ስራ ፈጠራ ይገኙበታል

ከዚህ በተጨማሪ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚገቡ ተማሪዎችም ተወዳድረው ለትምህርት የሚረዳቸውን የገንዘብ ሽልማት ያገኛሉ። ይህ ሽልማት በዋናነት በካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ያማከለ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአሜሪካ ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን መሸለሙ የሚታወቅ ነው። ስለዚህ በአጠቃላይ በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ማለት እንችላለን።

የዘንድሮውን ሽልማትን ከዚህ ይመልከቱት: አባይ ሚዲያ

ለበለጠ መረጃ ድህረ ገፁን ይመልከቱ። ቢቂላ አዋርድስ

Historical Dictionary of Ethiopia

Advertisements