ስለ ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ ማወቅ የሚገባዎትን በስድስት ሰንጠረዦች እነሆ (ቢቢሲ)

ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር በቃላት ጦርነት በተጠመደችበት በዚህ ወቅት፤ ሰሜን ኮሪያውያን የሃገራቸው ከምዕራባዊያን ጋር ስለገባችበት ውዝግብ ያላቸው ግንዛቤ ምን እንደሚመስል ማወቅ አስቸጋሪ ነው። በዚህ ክፍለ ዘመን ሃገሪቷ ከተቀረው ዓለም እጅጉን ተነጥላለች። የህዝቡን የአኗኗር ሁኔታ ሊያሳዩ የሚችሉ አሃዞችን ማግኘት አስቸጋሪ ቢሆንም ኑሮ በሰሜን ኮሪያ ውስጥ ምን እንደሚመስል ሊያሳዩን የሚችሉ መረጃዎች አሉ።


ስርወ-መንግሥት እና ዲሞክራሲ

ኪም ኢል-ሱንግ እአአ በ1948 ዓ.ም ሰሜን ኮሪያን ከመሠረቱ በኋላ ከአባት ወደ ልጅ በሚያልፍ የስልጣን ርክክብ ሃገሪቷን ከተመሰረተች አንስቶ እስካሁን እያስተዳደሯት ይገኛሉ።

በዚህ ጊዜ ውስጥ ደቡብ ኮሪያ ስድስት የሪፐብሊክ መንግሥታት ተቀያይረውባታል። አብዮትን አስተናግዳለች። ሁለት መፈንቅለ-መንግሥት ተካሂደውባታል። እንዲሁም ነጻና ገለልተኛ የሆኑ ምርጫዎችን አስተናግዳለች። በአጠቃላይ 12 ፕሬዝዳንቶች ለ19 ዙር ሃገሪቷን አስተዳድረዋል።


የተንቀሳቃሽ ስልክ ባለቤት በዛት

ሦስት ሚሊዮን ተንቀሳቃሽ ስልክ ብዙ ሊመስል ይችላል። 25 ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርባት ሃገር ውስጥ ግን 3 ሚሊዮን ማለት አንድ አስረኛው ነዋሪ ብቻ ነው ተንቀሳቃሽ ስልክ ያለው። አብዛኛው የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች በዋና ከተማዋ ፕዮንግያንግ አካባቢ የሚኖሩ ናቸው።

በተቃራኒው በደቡብ ኮሪያ የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ቁጥር 51 ሚሊዮን ገደማ ሲሆን ይህም ከሰሜን ኮሪያ ህዝብ ቁጥር በላይ ነው።

ለረጅም ዓመታት ከግብጽ ኩባንያ ጋር በመተባበር የሰሜን ኮሪያው ኮሮሊንክ የተባለው የቴሌኮምዩኒኬሽን ድርጅት በብቸኝነት አገልግሎት ሰጪ ሆኖ ቆይቷል። የግብጹ ኩባንያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለው ግንኙነት ሲሻክር ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደንበኞቹ መረጃ ከቁጥጥሩ ውጪ እንደሆነ ይፋ አድርጎ ነበር።

የአሜሪካ-ደቡብ ኮሪያ የጥናት ተቋም አደረኩት ባለው ጥናት መሠረት አዲስ የአየር ሰዓት ከመግዛት ይልቅ አዲስ መስመር ማውጣት ይረክሳል። በሃገሪቷ ውስጥም ከፍተኛ የሆነ የተንቀሳቃሽ ስልክ እጥረት አለ።

አብዛኛው የሰሜን ኮሪያ ህዝብ በሃገር ደረጃ ብቻ የሚሰራውን የኢንተርኔት አገልግሎት ይጠቀማል። እአአ በ2016 የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው በሃገሪቷ ውስጥ 28 የኢንተርኔት አድራሻዎች ብቻ ይገኛሉ።


የሁለቱ ኮሪያዎች የወንዶች ቁመት

የሰሜን ኮሪያ ወንዶች ከደቡብ ኮሪያዎች በቁመት እንደሚያጥሩ ጥናቶች አመላክተዋል።

በሁለቱ ሃገራት ወንዶች መካከል በአማካይ ከ3 እስከ 8 ሴ.ሜ ልዩነት አለ።

ጥናቱን ያካሄዱት ፕሮፌሰር በሁለቱ ሃገራት ወንዶች መካከል የተፈጠረው የቁመት ልዩነት፤ የዘረ መል ልዩነት አይደለም። ምክንያቱም የሁለቱም ሃገር ዜጎች አንድ ህዝብ ናቸው። ልዩነቱ የተፈጠረው በምግብ እጥረት ሳቢያ ነው ብለዋል።


የሁለቱ ኮሪያዎች የመንገድ ንጽጽር

ከሰሜን ኮሪያ ዋና ከተማ ፕዮንግያንግ የሚገኙ ምስሎች ሰፋፊ እና ብዙ የትራፊክ እንቅስቃሴ የማይታይባቸውን ጎዳናዎች ያሳያሉ። ገጠራማው የሃገሪቷ ክፍል ደግሞ የተለየ መልክ ነው ያለው።

እአአ 2006 ዓ.ም የነበረ አሃዝ እንደሚያሳየው ሰሜን ኮሪያ 25554 ኪ.ሜ መንገድ ቢኖራትም ከዚህ ውስጥ 3 በመቶው ብቻ ነው አስፋልት።

ከዚህ በተጨማሪም ከ1000 የሃገሪቱ ዜጎች 11 በመቶው ብቻ ናቸው መኪና ያላቸው።

አውቶቡስ ቆመው የሚጠብቁ መንገደኞችImage copyrightGETTY IMAGES
አጭር የምስል መግለጫበሰሜን ኮሪያ የሕዝብ መጓጓዣ እጥረት አለ

የሰሜን ኮሪያ ወነኛ ምርት የከሰል ድንጋይ ነው

ሰሜን ኮሪያ ወደ ውጭ በምትለከው የድንጋይ ከሰል ምርት ምጣኔ ሃብቷን ትደግፋለች። አብዛኛው የሰሜን ኮሪያ የድንጋይ ከሰል ወደ ቻይና ነው የሚላከው።

እአአ እስከ 1973 ዓ.ም ድረስ የሁለቱ ኮሪያዎች የሃብት መጠን ተመጣጣኝ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ደቡብ ኮሪያ እንደ ሳምሰንግ እና ሃዩንዳይን የመሳሰሉ ግዙፍ ኩባንያዎችን በመያዝ ከዓለማችን ቀዳሚዎቹ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች አንዷ ስትሆን፤ ሰሜን ኮሪያ ግን በአምባገነናዊ ሥርዓት ውስጥ ሆና እንደ 1980ዎቹ እየኖረች ትገኛለች።


የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ አቋም

በህዝብ ቁጥር ብዛት ሰሜን ኮሪያ ከዓለማችን 52ኛ ደረጃን ስትይዝ በሠራዊት ብዛት ግን ከዓለም 4ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ይገመታል።

ከሃገሪቷ አጠቃላይ ምርት ውስጥ 25 በመቶ የሚሆነው ለሃገሪቷ ጦር ኃይል የሚውል ነው። በአጠቃላይ ሁሉም የሰሜን ኮሪያ ወንድ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የጦር ልምምድ ያደርጋል።

እ.አ.አ በ1990 በተከሰቱት ተደጋጋሚ ድርቆች ምክንያት የሰሜን ኮሪያ የእድሜ ጣሪያ ዝቅ ብሏል።

እአአ 2017 የደቡብ ኮሪያ የወሊድ መጠን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሃገሪቷ ላለፉት አስር ዓመታት ያክል የወሊድ መጠንን ከፍ ለማድረግ እየጣረች ትገኛለች።

የደቡብ ኮሪያ መንግሥት ወሊድን ለማበረታታት ለወላጆች በስጦታ መልክ ገንዘብ በመስጠት፣ በወሊድ ጊዜ ለአባቶች ረዥም የዕረፍት ጊዜን በመፍቀድና የመሃንነት ህክምና በማድረግ ከ70 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጓል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: