የሳዑዲ ሴቶች ማድረግ የማይፈቅድላቸው ነገሮች

በምድራችን ሴቶች እንዳያሽከረክሩ በመከልከል ብቸኛዋ ሃገር የነበረችው ሳዑዲ አረቢያ ከንጉሱ በመጣ ትዕዛዝ ዕገዳው በዚህ ሳምንት እንዲነሳ እና ከሚመጣው ሰኔ ጀምሮ እንዲተገበር አድርጋለች። ምንም እንኳ ሃገሪቱ ይህን ውሳኔ ብታስተላልፍም አሁንም የሳዑዲ ሴቶች በርካታ ነገሮችን በራሳቸው ከማድረግ የታገዱ ናቸው።
የሳዑዲ ሴቶች ከታች የተጠቀሱትን ነገሮች ለመፈፀም የወንዶችን ይሁንታ መጠየቅ ይጠብቅባቸዋል።

  • ለፓስፖርት ማመልከት
  • ከሳዑዲ ውጭ ለመጓዝ
  • ትዳር ለመያዝ
  • የባንክ ሒሳብ ለመክፈት
  • ንግድ ለመጀመር
  • አስቸኳይ ያልሆነ ቀዶ-ጥገና. . .

ከመመስረቷ ጀምሮ ሳዑዲ አረቢያ ‘ዋሃቢዝም’ በተባለው የእስለምና ሕግ የምትመራ ሃገር ናት። በሃገሪቱ እ.አ.አ. በ1979 ከተከሰተው ብጥብጥ በኋላ ሳዑዲ ይህን ሕግ አጥብቃ መተግበር ጀመራለች።

በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሃገራት ሳዑዲ እኩልነት የማይትባት ሃገር ተብላ እንድትፈረጅም ሆኗል። በ2016 የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ባወጣው ደረጃ ከየመን እና ሶሪያ በመለጠቅ ሳዑዲን በመካከለኛው ምስራቅ እኩልነት ያልሰፈነባት ሃገር አድርጎ አስቀምጧታል።

‘አንድ ወንድ እኩል ይሆናል ሁለት ሴት’

ሳዑዲ የምታራምደው የሞግዚትነት ስርዓት እጅጉን ትችት እየደረሰበት ይገኛል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ‘ሂዩማን ራይትስ ዋች’ ሳዑዲ “ሴቶቿን የራሳቸውን ውሳኔ መወሰን የማይችሉ ሕጋዊ አናሳዎች አድርጋለች” ሲል ይወቅሳል።

እንዲህም ሆኖ ይህንን ጭቆና በመቃወም ድምፃቸውን ያሰሙ ሳዑዲያውያን ሴቶች ግን አልጠፉም። ሴቶች በግላጭ በወንድ ሳይታጀቡ በማያራመዱበት ሃገር ይህንን ማድረግ ቀላል እንዳልሆነ መገመት አያዳግትም።


Yves Rocher 24H Rich Hydrating Cream


የሳዑዲ ፍትህ ስርዓት በይፋ ሴቶች ላይ መድልዎ ያሳያል። በዚህ ጉዳይ እስላማዊ ሕግን የሚከተሉ ሃገራት ስርዓቱ ‘አንድ ወንድ እኩል ይሆናል ሁለት ሴት’ ነው ሲሉ ተቺዎች ይወቅሳሉ።

ለሳዑዲ ሴቶች ከትዳር አጋሮቻቸው ያፈሩትን ልጅ በፍቺ ወቅት የማሳደግ መብት ለማግኘትም እጅግ አዳጋች ነው። በተለይ ደግሞ ሴት ልጅ ከሆነች ዘጠኝ ዓመት ለወንዶች ሰባት ዓመት ካለፋቸው እና እናት የሌላ ሃገር ዜጋ ከሆነች የአሳዳጊነት መብት ማግኘት የማይታሰብ ነው።

እንዲህም ሆኖ በሳዑዲ ከሴቶች ጋር በተያያዘ የሚያስገርሙ ነገሮች ልንሰማ እንችላለን። ከ2015 ጀምሮ ሴቶች መምረጥ እንዲችሉ ሆኗል። ማንኛውም የሳዑዲ ዜጋ፤ ሴትም ሆነ ወንድ፤ እስከ 15 ዓመታቸው ትምህርት የመማር ግዴታ አለባቸው። ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቁ ሴቶች ቁጥርም ከወንዶች የላቀ ነው።

ከጠቅላላው የሳዑዲ የሥራ ሃይል 16 በመቶው ሴቶች ናቸው። ሆኖም በሥራ ቦታ ምን መልበስ እንዳለባቸው መወሰን ግን አይችሉም።

‘አባያ’ የተባለውን ልብስ በመልበስ የሳዑዲ ሴቶች መላ አካላቸውን መሸፈን አለባቸው።

በሳዑዲ ለሴቶች ብቻ ተብለው የተዘጋጁ ቦታዎችን ማየት የተለመደ ነው። በመገበያያ ቦታዎች ለምሳሌ አባያ ለሚለብሱ ሴቶች ብቻ የተዘጋጁ ክፍሎች ውስጥ አባያ የማይለብሱ ሴቶች ከተገኙ በሃይማኖታዊ ፖሊሶች ተይዘው ሊታሰሩ ይችላሉ።

የሳዑዲ ዜጋ ያልሆኑ ዜጎች አባያ መልበስ አይጠበቅባቸውም። ሙስሊም ካልሆኑም ራሳቸውን የሚሸፍን ነገር ባይደርቡም ችግር የለውም።

በሌላው የዓለም ክፍልስ. . . ?

ጥቂት የዓለማችን ሃገራት ሴቶችን በተመለከተ መሰል ስርዓቶችን በመዘርጋት ይታወቃሉ። ከዛም አለፍ ሲል አንዳንድ ሃገራት ሴቶች በጣም አስገራሚ ነገሮችን እንዳያደርጉ ያግዳሉ። እስቲ ጥቂቶቹን እንመልከት።

ቻይና፦ የቻይና ትምህርት ሚኒስቴር ሴቶች ማዕድን ጥናት፣ የምድር ውስጥ መተላለፊያ ምህንድስና እንዲሁም የዳሰሳ ጥናት እንዲማሩ አይፈቀድም። ሚኒስትሩ መሰል የትምህርት ዓይነቶች ለሴት ክብር የላቸውም ሲሉ ይደመጣሉ።
እስራኤል፦ በእስራኤል ባል ካልፈቀደ ሚስት የፍቺ ጥያቄ ማቅረብ አትችልም። ምክንያቱም ፍርድ ቤቶች በሃይማኖታዊ ስርዓት ስለሚተዳደሩ። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ጊዜ እንግሊዛዊው ዳኛ “ባልሽ በትዳር መቆየት ስለፈለገ ፍቺውን ውድቅ አድርገነዋል” ብሎ መበየኑ አይረሴ ነው።

ሩስያ፦ አናፂነት፣ እሳት አደጋ ሰራተኛ መሆን፣ ባቡር ማሽከርከር እንዲሁም መርከብ መንዳት በሩስያ ለሴቶች የተፈቀዱ አይደሉም። ቀጣሪዎች ለሴቶች የሚሆን ምቹ ሁኔታ አመቻችተናል ካሉ በመሰል ድርጊቶች ሴቶችን ማሰማራት ይችላሉ።

በኢንዶኔዥያ ከወንዶች ኋላ ተቀምጠው በሞተር ብስክሌት የሚሄዱ ሴቶች እግሮቻቸውን በአንድ በኩል ብቻ አድርገው መጓዝ አለባቸው። በሌላ አነጋገር እግሮቻቸውን በሁለቱም የሞተር ብስክሌቱ አቅጣጫ ዘርግተው መሄድ አይችሉም።

በሱዳን ደግሞ ሱሪ አድርገው የተገኙ ሴቶች ለግርፊያ ቅጣት የተጋለጡ ናቸው።


Yves Rocher AOC Olive Oil Silky Body Cream

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.