⚡የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የብቃት ምዘና ፈተናን የተቃወሙ ከ1400 በላይ ተማሪዎችን ከግቢው እንዲወጡ አደረገ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ተቋም ለ4ተኛ ዓመት ምህንድስና ተማሪዎች የሚሰጠው የብቃት ማረሆሊስቲክ) ፈተና በተማሪዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል።


የተቋሙ 4ተኛ ዓመት ምህንድስና ተማሪዎች የምዘና ሰርዓቱ አግባብነት የለውም በማለታቸው ከ1400 በላይ የሚሆኑቱ ከግቢው እንዲወጡ ተደርጓል።
በስልክ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ለፈተና ዝግጅት በቂ ጊዜ አልተሰጠንም፤ የምዘና ስርዓቱም አዲስ እና አግባብነት የሌለው ነው ብለዋል። ስሙ አንዳይጠቀስ ያሳሰበን ተማሪ ለቢቢሲ አንደተናገረው ”የብቃት ማረጋገጫ (ሆሊስቲክ) ፈተና ከ5 ቀናት በኋላ አንደምንወስድ ነበር በማስታወቂያ የተነገረን። ይህ ደግሞ ለፈተናው ዝግጅት ለማድረግ በቂ ጊዜ አይደለም። ለምሳሌ ለሲቪል ምህንድስና ተማሪ የሆሊስቲክ ፈተናው የሚወጣው ከ26 ኮርሶች ውስጥ ነው። በ5 ቀናት ውስጥ ደግሞ 26 ኮርሶችን ከልሶ ለፈተና መዘጋጀት በጣም ከባድ ነው” ይላል።


ከዚህም በተጨማሪ ተማሪዎቹ የአመዛዘን ስርዓቱ ከዚህ ቀደም ከምናውቀው ተቀይሯል ሲሉ ቅሬታ ያሰማሉ። በስልክ ያነጋገርናቸው ተማሪዎች ሲያስረዱ ”ከዚህ በፊት የነበረው የአመዛዘን ስርዓት ‘በግሬዲንግ ሲስተም’ ነበር ይህም ማለት የፈተናው ውጤት የሚገለፀው ከ ‘A-F’ ነበር። የ2009 ዓ.ም ተማሪዎችም በዚሁ የምዘና ስርዓት ነበር ያለፉት። ዛሬ ላይ ግን ይህ ቀርቶ አልፏል ወይም ወድቋል (Pass or Fail) እንዲሆን ተደርጓል ይላሉ። ይህም የፈተና ውጤታችን ከ50% በታች ከሆነ አንድ ዓመት ወደ ኋላ አንድንቀር ይደረጋል። ከዚህ በፊት ግን ‘F’ ያመጣ ተማሪ እንኳ ወደ ልምምድ ወጥቶ በቀጣዩ ዓመት አንዲፈተን ይደረጋል” ሲሉ ያስረዳሉ።


Get a Free Gift with any purchase.

አሁን ተማሪዎቹ ያሉበት ሁኔታ

ከ1400 በላይ የሚሆኑት የ4ኛ ዓመት ምህንድስና ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ፈተናውን መውሰድ የነበረባቸው መስከረም 18 ነበር። ለፈተና እንደማይቀመጡ ለዩኒቨርሲቲው ካሳወቁ በኃላ ከዩኒቨርሲቲው ያገኙት የነበረው የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት ተቋርጦ ካሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ በፖሊስ ግቢውን ለቀው አንዲወጡ ተደርገዋል።

”ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ዘመድ ያላቸው ዘመዶቻቸው ጋር ሄደዋል። ዘመድ የሌለን ደግሞ በቤተክርሰቲያን ግቢ ውስጥ ተጠልለን

ብንገኝም ፖሊስ ካለንበት ቤተክርሰቲያን ወጥተን ወደ የቤተሰቦቻችን እንድንሄድ እያስገደደን ነው።”

ዩኒቨርሲቲው የመጨረሻ ውሳኔውን እስኪያሳውቀን ድረስ የትም አንሄድም የሚሉት ተማሪዎቹ ዛሬ ማክሰኞ አርፈውበት ከነበረበት የአቡነ ገብረ-መንፈስ ቅዱስ ቤተክርሰቲያን አዳራሽ ውስጥ ፖሊስ እንዳስወጣቸው እና ማረፈያ ቦታ እየፈለጉ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“ትምህርት ቤቱ በወረደ ደረጃ አስተምሮን ከኛ ትልቅ ነገር እየጠበቀ ነው” ሲሉም ያማርራሉ።

ዶ/ር ንጉስ ጋቢዬ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ሲሆኑ ‘ፈተናውን ለመፈተን የተሰጠን ጊዜ አጭር ነው’ የሚለው ምክንያት ሊሆን አይችልም ይላሉ። ”የ2009 ዓ.ም የትምሀርት ዘመን ከመጠናቀቁ በፊት ለተማሪዎቹ ስለ ፈተናው ገለፃ አድርገንና ቅፅ አስሞልተን ነው ወደ ቤተሰቦቻቸው የሄዱት” ይላሉ ዶ/ር ንጉስ።

ከዚህ በተጨማሪም የአመዛዘን ስርዓቱ በፊትም የነበረ እንደሆነ የሚያስረዱት ዶ/ር ንጉስ ተማሪዎቹ ፈተና ለመፈተን ፈቃደኛ ስላልሆኑ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል ይላሉ። ”የመንግሥት በጀት ወጪ የሚሆነው ለሥራ ብቻ ነው። ተማሪዎቹም ለመፈተን ፍቃደኛ ስላልሆኑ ከዩኒቨርሲቲው ምንም አገልግሎት እንደማያገኙ አሳውቀን ግቢውን ለቀው እንዲወጡ አድርገናል። ከዚህ በኋላ በአካዳሚክ ሕጉ መሠረት ነው የሚዳኙት” ብለዋል።

ቢቢሲ


Obtenez un cadeau gratuit avec toute commande !

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.