ዊሊያም ቲንዴል፦ “የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ አባት”

(በዶ/ር Girma Bekele)

መጽሐፍ ቅዱስን ለትውልዱ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በመተርጎሙና በድነት፣ በቤተ ክርስቲያን ማንነትና ተልእኮ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ፊት ለፊት በመቃወሙ፣ በአደባባይ በታሰርበት ቋሚ እንጨት ላይ በማገዶ እሳት ጋይቶ ከመሞቱ በፊት፣ የዊልያም ቲንዴል የመጨርሻ የስቃይ ጸሎት፣ “ጌታ ሆይ የእንግሊዝ አገርን ንጉሥ ዐይኖች ክፈት” የሚል ነበር።
Bose Syst�me d?enceintes multim�dias Companion�50
ቲንዴል በቤተ ክርስቲያን የተሃድሶ ታሪክ ውስጥ “የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ አባት” በመባል እስከ ዛሬ ድረስ ይታወሳል። በ 1401፣ የእንግሊዝ ፓርላማ፣ በሮማ ቤተ ክርስቲያን አተርጓጎም በኑፋቄነት የተወነጀለ ሰው በእሳት ጋይቶ እንዲሞት የሚያዝ ዐዋጅ “de Haeretico Comburendo—“on the burning of heretics” አወጣ። ከሰባት ዓመት በኋላ፣ ይኽንኑ ዐዋጅ ያከርረውና መጽሐፍ ቅዱስን ወደ እንግሊዝኛ በሙሉ ሆነ በከፊል መተርጎም በሕግ የሚያስቀጣው “የኦክስ ፎርድ መተዳደሪያ – the Constitutions of Oxford” በካንትበሪው ሊቃነ ጳጳስ፣ ቶማስ አርንዴል (Archbishop of Canterbury, Thomas Arundell) ወጣ። (Brian Moynahan, God’s Bestseller, xxii):

Yves Rocher Loose Pearls-Intense illuminating effect - Taupe

በዚሁ ዐዋጅ መሠረት፣ ልጆቻውን በእንግሊዝኛ የተጻፈ የጌታችን ጸሎት (The Lord’s Prayer) በማስተማራቸው ብቻ፣ በኮቨንትሪ ከተማ የነበሩ አሥራ አንድ አማኞችን፣ የሮም ቤተ ክርስቲያን በአደባባይ አቃጥላቸዋለች። “ያለፓፓ (Pope) ከመኖር ይልቅ፣ ያለ እግዚአብሔር ቃል መኖር ይሻላል” በሚባልበትና የፓፓው ሥልጣን ፍጹማዊ በነበረበት ወቅት ነበር፣ ዊልያም ቲንዴል በአንዲት ነፍሱ በወራራድ፣ ይህን በእግዚአብሔር ዘንድ ሕገ-ወጥ የሆነ ዐዋጅ ለመሻር የተነሳው። “ከአናሳዎቹ (minority) ነኽ፤ አይነኬውን የሮማ ቤተ ክርስቲያን ውቅር እንዴት ብቻህ ትችለዋለህ?” ላሉት ተስፋ አስቆራጮች፣ ቲንዴል ምላሹ እንዲህ የሚል ነበር፦


Kaspersky Lab United States | Visit the website.

“ፓፓውንና ሕገ-ወጥ ሕጎቹን፣ እቃወማለሁ፤ እግዚአብሔር ዕድሜ ቢያርዝምልኝ፣ [በዘመኔ ሁሉ] ተራ ገበሬ ሁሉ [ክርስቶስን ከጋረዱት] ካህናት ይልቅ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የበለጠ እንዲያውቅ አደርጋለሁ” (Tony Lane, Book of Christian Thought, 154).

ቲንዴል የጸጋ ምስጢር የገባው የጌታ ባሪያ ነበር። ጸጋ በአዳም ውስጥ ከተሰካንበት ክፋት ነቅሎ፣ በክርስቶስ መልካምነት ላይ ሰክቶናል። የበረሓ ከሆነው የወይራ ዛፍ ተቆርጠን፤ ተፈጥሮአችን ወዳልሆነው ወደ መልካሙ ወይራ ያስገባን ብቃታችን ጸጋ ብቻ ነው። ዓለም ሳይፈጠር በፊት፣ እግዚአብሔር በክርስቶስ አየን፣ እንዲሁ ወደደን፣ መረጠን። ወንጌል በትክክልና በሥልጣን ሲሰበክ፣ ይህን መለኮታዊ ነጻ አውጭ እውነት ማንም ሊያጠፋው በማይችል መልኩ በሰው ልብ ውስጥ ይበራል። ከክርስቶስ ጋር ብዙሃን መሆኑ የገባው ቲንዴል፣ በውስጡ የበራውን ይህን የወንጌል እውነት አምቆ ሊይዘው አልቻለም። በሙት ሃይማኖተኝነት ቀንበር ተጠፍሮ፣ በክርስቶስ መካከለኛና ብቸኛ አዳኝነት የሚገኘውን ሕይወት ሳያገኝ፣ ወደ ሲኦል የሚጋዘው ትውልድ ጉዳይ እጅግ እረፍት ነሳው። ምንም እንኳን የስመ-ጥሩ ኦክስ ፎርድ ምሩቅ፤ የሰባት ቋንቋዎች ባለሙያ፣ እንዲሁም የሥነ-መለኮትና ፍልስፍና ፕሮፌሰር ሆኖ ኑሮ የተመቸው ወጣት ቢሆንም፣ ስለ ወንጌል እውነት ሁሉን እንደ ረብ ቆጠረ! እናም በአንዲት ነፍሱ ፈረደ – የትውልዱን የሞት አቅጣጫ ለመቀየር!


“መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ በብዙ ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የመሰከርህለትንና የተጠራህበትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ።” (1 ጢሞ 6:12) የሚለው ቃል፣ የቲንዴል ትጉህነት መሠረት ነበር። በ1524፣ በ30 ዓመቱ፣ የሞት ዐዋጅ ከታወጀበት የትውልድ አገሩ ላይመለስ ወደ ቤልጅየም፣ ብራስልስ ተሰደደ። በዚሁ የስደት ወቅት ነበር ከእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋዎች፣ ቅዱስት መጻሕፍትን ወደ እንግሊዝኛ መመለስ የጀመረው። ከ85% በላይ የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ምንጩ፣ የቲንዴል ታማኝና ጥንቃቄ የተሞላበት ትርጉም ሥራ ነው። በቀን 12 ሰዓት በላይ ይተጋ ነበር። ዕለተ እሁድ የወንጌል ሰበካ ቀኑ ሲሆን፣ ሰኞና ቅዳሜ ክርስቲያን ስደትኞችንና መንገድ ላይ የወደቁ ችግረኞችን በመጎብኘት ምጋቢያዊ አገልግሎት ይሰጥ ነበር። ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቷልና!

መከራው ብዙ ነበር። ነፍሱ አንደ ወፍ እንድትታደን ዐዋጅ በወጣባቸው የተለያዩ የአውሮፓ ግዛቶች፣ በሰቀቀን እየኖረ፣ በለሌትና ቀን ትጋቱ፣ የጀመረውን ትርጉም ሥራ ማጠናቀቅ ነበር። ባለቀ ሰዓት፣ እግዚአብሔር ጣልቃ እየገባለት ከብዙ የሞት ወጥመዶች አምልጧል። “ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤ በቤቴ ጒልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።” (መዝ 102:7)፤ ያለባቸው ብዙ ጨለማዎች አሳልፏል። አዲስ ኪዳንን በድብቅ እንደኮትሮባንድ ወደ እንግሊዝ በማስገባት በነፍሳቸው ከተወራረዱት መካከል የቅርብ ወዳጁ ጆን ፍሪት (John Frith) በጥቆማ ተይዞ በአደባባይ ተቃጥሏል። ዕድሜው 28 ነበር! ሌሎችም የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ወይንም ድነት በጸጋ ብቻ፣ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን የመጨረሻ ሥልጣን ቅዱስ ቃሉ ብቻ መሆኑን የሚያስገነዝቡ ጽሑፎችን ሲያነቡ የተገኙ፣ የሄነሪ ስምንተኛ የሮም ቤተ ክርስቲያም አማካሪና ቻንስለር በነበረው ጨካኙ ቶማስ ሙር ትዕዛዝ አልቀዋል። በሞት ጥላ ውስጥ እያለፈ የተረጎመውን ሁለት ሦስትኛ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሮም ቤተ ክርስቲያን በአራት እጥፍ ዋጋ በድብቅ እየገዛች ታቃጥል ነበር። ብዙ ጊዜ፣ ለሊትና ቀን የደከመባቸው ረቂቅ የትርጉም ሥራዎቹ፣ ወዳጅ በመምስል በቀረቡ ሰዎች ተሰርቆበታል። በዚህ ሁሉ ልቡን እንደ ዳዊት በአምላኩ በእግዚአብሔር አበረታ እንጂ ተስፋ አልቆረጠም። እናም እንዲህ አለ፦


“በመከራና በሥቃይ እንጂ፣ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግቢያ ሌላ መንገድ የለም። ክርስቶስ ኀጢአት አላደረገም፣ አልበደለም፣ እስከ መስቀል ሞት ድረስ በጽድቅ መከራን ስለእኛ በትዕግሥት ተቀበለ። ልክ እንደዚሁ ክርስቶስን መስሎ በጽድቅ የሚሄድ አማኝ ሁሉ መከራን መቀበሉ የግድ ነው። በሁሉ ነገር፣ ሞትን ጨምሮ ክርስቶስን ልንመስል ተጠርተናልና!”


በጤና መቃወስ፣ በብችኝነት፣ በራብ፣ በብርድና በስደት ተንከራቷል። በመጨረሻም ይሁዳ፣ ጌታች ኢየሱስ ክርቶስን በመሳም አሳልፎ እንደሰጠው፣ የቅርብ ወዳጅና የራእዪ አጋዥ በመምሰል በቀረበው ሄነሪ ፊሊፕስ፣ በአንትዎርፕ ከተማ ተከዳ። ለሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት አሳልፎ ሰጠው። ለ 18 ወራት የሞት ፍርዱን፣ እየተጠባበቀ ባለበት ወህኒ ቤት ሳለ፣ ለአንድ ባለሥልጣን እንዲህ ብሎ ጽፎ ነበር፦

“. . . ወህኒ ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜ የምቆይ ከሆነ፣ የተወርሰብኝ የግል ንብረት እንዲመለስልኝ እማጸናለሁ። ብርዱ አጥንቴ ውስጥ ዘልቆ ግብቷል። ሳል ደርቴን አቁሱሎታል፤ እግሮቼ ተኮማትረዋል። ያለልዋጭ የለበስኩት አንድ ልብስ ሳስቶ፣ እላዬ ላይ አልቋል . . . የራስ የሱፍ ኮፍያዬ፣ ካፖርቴና የእግሬ ብርድ ልብስ እንዲመለሱልኝ በትህትና እጠይቃለሁ። ለሊቱን በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ማሳለፍ፣ የብቸኝነት ጭንቀት ፈጥሮብኛል፤ ኩራዝ ይፈቀድልኝ። ከሁሉም በላይ ልመናዬ፣ የእብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰዋሰዋስውና መዝገበ ቃላት እንዲመለሱልኝ ነው። ሆኖም፣ ፍርድ የተቆረጠና በቅርብ ጊዜ ተፈጻሚ የሚሆን ከሆነ፣ ባለሁበት ሁኔታ ለክርስቶስ ክብር የእግዚአብሔርን ፈቃድ በትዕግሥት እጠብቃለሁ።” (David Daniell, William Tyndale: A Biography, 379).

ከ12 የስደት ዓመታት በኋላ፣ 6 October 1536 በብራስልስ በአደባባይ፣ በጠብደል ሕግ አስፈጻሚ ወታደር አንገቱ ታንቆ፣ ነፍሱ ሳትወጣ በእሳት ተማግዶ ወደ ዘላላም ክብር ሄደ። የመጨረሻ ጸሎቱም “ጌታ ሆይ የእንግሊዝ አገር ንጉሥ ዐይኖች እባክህን ክፈት” የሚል ነበር። 42 ዓመቱ ነበር! ሆኖም ከሦስት ዓመት በኋላ ትንሣዔ መጣ። የሞት ዐዋጁን ያወጣው ሄነሪ ስምነተኛ፣ ዐዋጁን ሽሮ፣ ለቲንዴል ትርጉም ሕጋዊ ዕውቅና በመስጠት “ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ” (The Great Bible) በመባል የሚታወቀውን አሳተመ። የቲንዴል ልብ ሙሉ ለሙሉ፣ የእግዚአብሔር ፈቃድና የወንጌል እውነት ምርኮኛ ነበር . . . የዘመኗን ቤተ ክርስቲያን ልብና አደባባይ የማረከው ምን ይሆን? የወንጌል ዐደራ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ በእጃችን የገባው፣ በብዙ ሰማዕት ተጸፎና በታማኝነት ተጠብቆ ነው። ይኽን ዐደራ አንዴት እየጠበቅን ይሆን? “ጌታ ሆይ፣ ለራሳቸው የሞቱ፣ ለስምህ የኖሩ ታማኝ ባሪያዎች አድርገን።
አሜን!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.