የተንጠለጠለው የካታሎንያ የነፃነት ጥያቄ

የስፔን መንግሥት በካታሎንያ መሪ ቻርለስ ፑይጅዲሞንት የተፈረመውን የነፃነት አዋጅም ሆነ ድርድርም አንቀበልም ብለዋል። የስፔን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር በበኩላቸው የካታሎንያ መሪ “የት እንዳሉና ወዴት እንደሚጓዙ የማያውቁ” ብለዋቸዋል።

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያኖ ራሆይ ቀጣዩ የመንግሥት ምላሽን ለመወሰን አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባም ጠርተዋል። ቻርለስ ፑይጅዲሞንት ማክሰኞ ቀን የነፃነት አዋጁን የፈረሙ ሲሆን፤ ተግባራዊነቱን ለጊዜው ወደ ጎን በመተው ደርድሮች እንዲካሄዱ ፈቅደዋል ።

የካታሎንያ ፕሬዚዳንት ነፃነትን ከማወጅ በተጨማሪ ተግባራዊ ከተደረገ ስፔንን ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ይከታታል የሚሉ ስጋቶች እየተሰሙ ነው።

በቅርቡ የተደረገውን ሕዝበ-ውሳኔ ተከትሎ ስፔን አለመረጋጋት ውስጥ ናት፤ በወቅቱም የስፔን ህገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ህገ-ወጥ በማለት ሕዝበ-ውሳኔውን እንዳልተቀበለው የሚታወስ ነው።

የካታሎንያ መሪ ቻርለስ ፑይጅዲሞንት ባርሴሎና ውስጥ ለፓርላማ በተናገሩበት ወቅት ምርጫው ነፃ የመሆን መብታችንን አረጋግጦልናል ብለዋል።

“በዓለም ላሉ አገራትና አለም አቀፍ ድርጅቶች የካታሎንያ ሪፐብሊክ ነፃና ሉዓላዊት አገር መሆኗን እንድታውቁ ጥሪ እናደርጋለን” ብለዋል።

ጨምረው እንደተናገሩትም የህዝቡ ፈቃድ ከማድሪድ መገንጠልን ቢሆንም ያፈጠጡት ግጭቶች እንዲቀዘቅዙ ፍላጎታቸውም እንደሆነ ተናግረዋል።

“የነፃነት አዋጁ ተግባራዊ የማድረጉን ጉዳይ ለጊዜው ያዝ እናድርገውና በሚቀጥሉት ሳምንታት ተደራድረን መስማማት እንችላለን። ይህንን ካላደረግን መፍትሄ ላይ የምንደርስ አይመስለኝም” በማለት ቻርለስ ፑይጅዲሞንት ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል።

በመቀጠልም ቻርለስ ፑይጅዲሞንትና ሌሎች የካታሎንያ መሪዎች የነፃነት አዋጁን የፈረሙ ሲሆን አዋጁ ህጋዊ ተቀባይነት እንዳለው ግልፅ አይደለም።

በባርሴሎና የነፃነት ደጋፊዎች ቻርለስ ፑይጅዲሞንትን የነፃነት ንግግሩን የደገፉ ሲሆን ከመደራደር ጋር ያላቸውን አቋም ከገለፁ በኋላ ብዙዎች ኃዘናቸውን ገልፀዋል።

የስፔን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሶራያ ሳኔዝ ደ ሳንታማሪያ ቻርለስ ፑይጅዲሞንት ያቀረቡትን በአለም አቀፍ አደራዳሪዎች አማካኝነት እንነጋገር የሚለውን ሀሳብም አልተቀበሉትም።

የስፔን የፍትህ ሚኒስትር ራፋኤል ካታላ መንግሥታቸው ሕዝበ-ውሳኔውም ሆነ ውጤቱ ህገ-ወጥ ነው የሚለውን አቋም አፅንኦት ሰጥተውበታል።

የነፃነት ጥያቄውን 90% የሚሆነው የደገፈው ሲሆን መራጩም ህዝብ 43 % እንደነበር የካታሎንያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የነፃነት ተቃዋሚዎች በበኩላቸው የተቃወሙ ሲሆን ጉዳዩም ከፍተኛ ደረጃ በመድረሱ ፖሊስ በጉዳዩ ገብቶበት ምርጫው እንዳይካሄድ ያደረጉት ሙከራ መጨረሻው ብጥብጥ ሆኗል።

ከማክሰኞ ቻርለስ ፑይጅዲሞንት ንግግር በፊት ተፅእኖ ፈጣሪ የሚባሉ ታላቅ ሰዎች እንደ የባርሴሎና ከንቲባ አዳ ኮላው ነፃነቱን ከማወጅ እንዲቆጠቡ ምክርን ለግሰዋል።

ካታሎንያ በስፔን ውስጥ ካሉት ግዛቶች በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገች ስትሆን ነገር ግን አሁን ከተነሳው ብጥብጥ ጋር ተያይዞ መቀመጫቸውን ካታሎንያ ያደረጉ ኩባንያዎች ለመውጣት አኮብኩበዋል።

የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ ካታሎንያ ከስፔን የምትገነጠል ከሆነ የአውሮፓ ህብረት አባልነቷ ያከትማል ሲል መግለጫ አውጥቷል።

Source: BBC

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.