ከዚህ ዘጋቢ ፊልም ልንወስደው የሚገባን ትልቁ ቁም ነገር መቼም ቢሆን የህዝብን ድምፅ ማድመጥና ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ ነው።

 • ኤርትራ በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ አገዛዝ የነበራት ጥያቄ: መገንጠል
  • የተሰጠው ምላሽ: ፌዴሬሽኑን በመተው ኤርትራን ወደ ክፍለሀገርነት ቀላቀሏት
  • የተሻለ ምላሽ: ፌዴሬሽኑን ማክበርና ለኤርትራ ህዝብ ነፃነት ለኤርትራውያን የራስገዝ ማመቻቸት
 • በደርግ የኤርትራ ጥያቄ:መገንጠል
  • የተሰጠው ምላሽ: ጦርነት ማወጅ
  • የተሻለ ምላሽ: የዲፕሎማሲ ስራ መስራትና ለነበረው የእኩልነት ጥያቄ ምላሽ መስጠት

ዛሬ ላይ የተደቀኑብን ችግሮች ከዚህ የተለዩ አይደሉም። በተገቢው ምላሽ ካልተሰጣቸው መልሰን የምንዘፈቀው ወደዚሁ ነው።

 • የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ
 • የአማራ ህዝብ ጥያቄ

ቀጥሎ ያለው ዘጋቢ ፊልም ከኤርትራውያን እይታ የተሰራ ቢሆንም ለዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ወሳኝ መልዕክት አለው። እንደሀገር እንድቀጥል የተሳሳትናቸውን ማረም አለብን።

Advertisements