ከሰሞኑ በኢንጂነር ቅጣው እጅጉ ላይ እየተራገበ ያለው ወሬ በጣም የሚረብሽና የሚያስደነግጥ ነው። እውነት ነው ወይስ እንዲሁ በተለምዶ ወሬ የሚያናፍሱ ተራ የሚዲያ ባለሙያዎች የተሰራ አሉባልታ?

በዚህ ላይ ብዙ ግዜ ማጥፋት ራሱ የነዚህን ተራ ባለሙያዎች ዝና ማግነን ይሆናል። ስለሆነም ከዚህ በታች በምታገኙት ከራሱ ከናሳ የመረጃ ቋት ከተቀመጠው የምርምር ወረቀት ላይ ቅጣው የናሳ እህት ኮንትራክተር ድርጅት ለሆነው ጄት ፕሮፐልሽን ላቦራቶሪ (Jet Propulsion Laboratory)ይሰራ እንደነበር የሚያሳው ቀውን እንደመጀመሪያ ማስረጃ ማየት ይቻላል።

ይህ ከዚህ በታች የተመለከተው የናሳ ሪፖርት የፊት ገፅ ነው። በቢሊዮን ዶላር በጀት የሚሰራ ስራ እና ለሚስጥራዊ ስራ የተመደቡ ሰዎች እንደቀጤማ በየቦታው መገኘት እንደማይችሉ መረዳት መቻል ይኖርብናል። በተለይም ይህ ሪፖርት የ1980 እአአ ሲሆን እንደዚህ አይነቱን መረጃ በሚስጥር ካቆዩት በኋላ ነው ለህዝብ በነፃ የሚለቁት።

nasajpl

በዚህ ሪፖርት ማጠናቀቂያ ላይ የሪፖርቱ ግልባጭ ከሚደረሳቸው ሰዎች መካከል ደግሞ ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ እንዳሉበት ያሳያል።

በሪፖርት ቁጥር 159307 (NASA Contractor Report)መሰረት ቅጣው እጅጉ ለናሳ ከሚሰሩት ኮንትራክተር ክፍሎች መሃከል በካሊፎርኒያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውስጥ በጄት ፕሮፐልሽን ላቦራቶሪ እንደሚሰሩ ከነቢሮ አድራሻቸው ተቀምጧል።

Jet Propulsion Laboratory
4800 Oak Grove Drive
Pasadena, CA 91103
Attn: Library, Mail Code 111-113
Edward Mettler, Mail Code T-1201
Kitaw Ejigu, Mail Code 158-244

nasajpl

በመጨረሻም እንዲህ አይነት እኩይ ተግባር ለሚያከባውኑ ጋዜጠኛ ነን ባዮች –> የራሳችሁን የቤት ስራ ስሩ በሏቸው።

Advertisements