“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ችግሩን ከምንጩ አይፈታውም” ምሁራን

ባህር ዳር፡የካቲት 19/2010 ዓ/ም

(አብመድ)የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሳምንት በፊት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ከምንጩ አይፈታውም ሲሉ ምሁራን ገለጹ::

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር የሆኑት አቶ ዘላለም እሸቱ በሀገሪቱ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚጋብዙ አካባቢዎች መኖራቸውን ቢያምኑም በሁሉም የሀገሪቱ ቦታዎች ላይ አዋጁን መጫን ተገቢ አይደለም ይላሉ:: መንግስት አካባቢዎችን ለይቶ ማውጣት ነበረበት፤ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚጋብዝ ሁኔታ ተፈጥሯል ቢባል እንኳ አዋጁ ችግሩን ከምንጩ የሚፈታው እንዳልሆነ ሙያዊ ትንታኔ ሰጥተዋል::

“ሀገሪቱ አሁን ያለችበት ሁኔታ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚጋብዝ በቂ ምክንያት የለውም” የሚሉት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር መምህሩ አቶ ስዩም ተሸመ በበኩላቸው አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው “የድንበር ወረራ፣ ህገ መንግስትን በኃይል ለመናድ አሊያም የበሽታ ወረርሽኝ ሳይሆን ህዝብ የሚያነሳው የመብት፣ የነፃነት፣ የዴሞክራሲና የፍትኃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ነው” ብለዋል::

መንግስት በአንድ በኩል እስረኛ እየፈታ በሌላ በኩል ለእስር የሚዳርግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ፍፁም ተቃርኖ ነው ሲሉም ገልጸዋል::

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ቃለወንጌል ምናለ ደግሞ “ከአዋጁ ውጭ ሌሎች የመፍትሔ መንገዶች ነበሩ” ይላሉ::

በመንግስት ተጀምሮ የነበረውን የፖለቲካ ምህዳር በማስፋት ለውጡ በግለቱ እንዲቀጥል ማድረግ፣ አዲስ ምርጫና ሁሉን አሳታፊ የሆነ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ ማሳለፍ ቢችል ችግሮችን መፍታት ይቻል ነበር ብለዋል::

በመሆኑም ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ለመቀየር በሰከነ መልኩ በውይይትና በመግባባት ላይ ተመስርቶ መፍትሔ ማፈላለግ ይጠይቃል ሲሉ ምሁራኖቹ ገልጸዋል::

በ2009 ዓ.ም በሀገሪቱ የነበረውን አለመረጋጋት ለማስቆም ለ10 ወራት ያህል ተግባራዊ ተደርጐ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተነሳ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተመልሶ ተግባራዊ የተደረገ ነው:: አዋጁ ለስድስት ወራት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከቀናት በኋላ ለተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል::

አብርሃም አዳሙ

በኩር ጋዜጣ የካቲት 19/2010 ዓ/ም ዕትም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.