የኢህአዴግ ምርጫ ትብብርን የሚያዳብር እንጂ የፉክክርን እና የዜሮ ድምር ጨዋታ ባይሆን ይመረጣል! – ዳንኤል ብርሃኔ

እስከዛሬ የተለመደው የኢህአዴግ ሊቀ-መንበር ምርጫ የአራቱ ፓርቲዎች ሊቀመናብርት በእጩነት ቀርበው ድምጽ የሚሰጥበት አካሄድ ነው። እርግጥ መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ እያሉ አብዛኛውን ድምጽ ያለችግር ይጠቀልሉት ስለነበር ምርጫው የሴሪሞኒ ያህል ነበር ማለት ይቻላል።

ስለዚህ ልማዳዊው አሰራር አደጋው ሳይታይ ቆይቷል። ዛሬ የተለየ ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ ገብተናል። ዛሬ የሁሉንም ድምጽ በቀላሉ የሚጠቀልል ሰው የለም። ዛሬ የብሔር ፉክክር ጦዟል። ዛሬ ለምርጫ የቀረቡት ብሔሮች እንዲመስል ሆኗል። ምርጫው የመሪ ሳይሆን የብሔር መስሏል። ይሄ ደግሞ ጤናማ አይደለም። ለዛሬም ለወደፊቱም።

ኢትዮጲያ የ80+ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሀገር ናት። እነዚህ ብሔሮች ተባብረውና ተደጋግፈው የሚሰሩበት እንጂ የማያገባቸው እንዲመስላቸው የሚያደርግ ድባብ መፍጠር አይጠቅምም።

ሁሉም ብሔሮች በአንድ ግዜ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ባይችሉም እንኳን ሁሉም እኩል የመመረጥ እድል ሊኖራቸው እንደሚችል የሚያመላክት አካሄድ ይገባል።

በዚህ መንፈስ በማሰብ፤ ልማዳዊው የኢህአዴግ የምርጫ አፈጻጸም ሊከለስ ይገባል ባይ ነኝ።

የኔ ፕሮፖዛል እንዲህ ነው:-

* የኢህአዴግ ምክር ቤት ይሰብሰብ፤ የምክር ቤቱ አባላት ከሁሉም ድርጅቶች ሁለት ወይም ከዛ በላይ እጩዎች – በድምሩ እስከ10 እጩዎች – ይጠቁሙ።

* ከዚያ በኋላ የኢህአዴግ ምክር ቤት የተወሰኑ ቀናት እረፍት ይውሰድ።

* በነዚህ ቀናት እጩዎቹ ራዕያቸውን ለምክር ቤቱ አባላት የሚያቀርቡበት ፓናል ነገር ይዘጋጅ። በግልም በቡድንም እያገኙ የማግባባት ስራ (lobby) ይስሩ።

* በመጨረሻ ምክር ቤቱ ተሰብስቦ ድምጽ ይስጥ።፡

* በመጀመሪያ ዙር 50%+1 ያገኘ እጩ ካለ አሸናፊ ይሆናል።

* አለበለዚያ ዝቅተኛ ድምጽ ያገኙ እጩዎች እየተቀነሱ በቀሩት መሀል ውድድር ይቀጥልና 50%+1 ድምጽ ያገኘ እጩ አሸናፊ ይሆናል።

የዚህ ሂደት ጠቀሜታ በርካታ ነው።

1) እጩ ተወዳዳሪ በብሔሩ ምክንያት ብቻ አያሸንፍም ወይም አይሸነፍም።

2) ከአንድ ብሔር ወይም ድርጅት ከአንድ በላይ እጩ ስለሚኖር ከብሔሩ ወይም ድርጅቱ ባሻገር የሰውየው ብቃትና ሀሳብ ቦታ ይኖረዋል።

3) እጩዎች የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላትን ድምጽ እንዲሰጡዋቸው ሲያግባቡ በሂደቱ ከራሳቸው ብሔር ወይም ድርጅት ያለፈ ትስስር ይፈጥራሉ።

4) በሂደቱ የተሻለው ሰው መመረጥ መቻሉ ብቻ ሳይሆን መተማመንን መተባበርን እና የሀሳቦች መዳበርን ያስገኛል።

ይህ አሰራር ጥሩ ውጤት ካመጣ፤ በሂደት ኢህአዴግ በታችኛው መዋቅርም በመተግበር በየደረጃው ትብብር እንዲዳብር ብቁ መሪዎች እንዲወጡ ሊያደርግ ይቻላል።

ጥሩ ውጤት ካላመጣም በቀጣይ ሌላ አማራጭ ይሞከራል።

መቼም “እገሌ ብሔር አሸነፈ” “እገሌ ብሔር ተሸነፈ” ከሚል አክሳሪ የዜሮ ድምር ጨዋታ የማይሻል ነገር የለም።

ዞሮ ዞሮ አብዛኛው ኢትዮጲያዊ የሚፈልገው አሁን ካለንበት ቀውስ ለማውጣት የድርጅትና የመንግስት መዋቅሮችን አስተባብሮ ለመስራት አቅሙና ፍላጎቱ ያለው መሪ እንጂ፤ የብሔር ፉክክር አይደለም።

በብሔር ከተኬደማ አፋር ወይም ጉሙዝ ከማንም ያላነሰ መብት አላቸው። ያ ደግሞ ማለቂያ የሌለው ነገር ነው።

ኢህአዴግ እንደዋዛ የጀመረውን ስልጣን በብሔር የመሸንሸን ጨዋታ አቁሞ፤ አስተባብረው ስራ መስራት የሚችሉ ግለሰቦች ወደፊት የሚወጡበት ስርአት ይዘርጋ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.