የቀጠና አንድና ሁለት ኮማንድ ፖስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈጸሚያ ዝርዝር መመሪያ ላይ ተወያዩ – ፋናቢሲ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀጠና ሁለት ኮማንድ ፖስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈጸሚያ ዝርዝር መመሪያና በቀጠናው እቅድ ላይ በሀዋሳ ከተማ ተወያየ።

የቀጠና ሁለት ኮማንድ ፖስት በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ በኦሮሚያ ሰባት ዞኖችና በአካባቢዎቹ ባሉ ዋና ዋና ከተሞች እና በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ሁለት ዞን እንዲደራጅ ተደርጓል።

ኮማንድ ፖስቱ እንደገለፀው በውይይቱ የየክልሎቹ እና ዞኖቹ የፀጥታ ዘርፍ እና የፖሊስ መመሪያ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል።

በዚህም ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ ዝርዝር መመሪያና በቀጠናው መመሪያውን ማስተግበሪያ እቅድ ላይ ምክክር ተደርጓል ነው ያለው።

በውይይቱ ህብረተሰቡ የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ የነበረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።

በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ እና ዙሪያው የቀጠና አንድ ኮማንድ ፖስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም በተመለከተ ውይይት አድርጓል።

በ14 ንዑስ ቀጠና ተደራጅቶ የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት አመራሮችና አባላት እንዲሁም የፀጥታ አካላት ሃላፊዎች ቀጠናው ባዘሃጀው እቅድ ላይ ተወያይተዋል።

የቀጠና 1 ኮማንድ ፖስት አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በፊንፊኒ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ ምዕራብ ሸዋ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች እንዲደራጅ ተደርጓል።

የቀጠና አንድ ኮማንድ ፖስት የህብረተሰቡን የመኖር ህልውና ለማረጋገጥ እና የሀገሪቱን ሰላም ለማስፈን የፀጥታ ሃይሉ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል።

የሀገርን ሰላምና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች ያለምንም ስጋት ከኮማንድ ፖስቱ ጎን በመቆም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ መጠየቁንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመላክቷል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.