ኤርሚያስ ለገሰ ስለ ጄነራል አበበ

ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖት ከፅሁፍ ወጥቶ በቪዲዬ ተደግፎ መጥቷል። ዘወትር እናት ድርጅቱ ህውሓት ጭንቅ ሲይዛት እየሮጠ የሚመጣው ጆቤ ዛሬም ማደናገሪያ፣ ማሸማቀቂያ እና አጀንዳ ማስቀየሺያ ቁም ነገሮችን ይዞ ብቅ ብሏል።

ወቅቱ ሙሉ በሙሉ በተቀየረበት ሁኔታ የጄኔራሉ ጠባብ ፍላጐት የማይሳካ ቢሆንም ለአፍ ማሟሻ ሊያገለግል ይችላል።

እነሆ ጄኔራሉ እንዲህ ይሉናል፣

#1-: ከ27 አመት በኃላ ብአዴን እና እነ አባዱላ ገመዳ የትግራይ የበላይነት አለ ብለው ሲያነሱ በጣም አፍርባቸዋለሁ። ድሮ እነ አባዱላ ይሄን ለማንሳት ይፈሩ ነበር ማለት ነው?

( እኔ: ብአዴን እና አባዱላ ትፈሩ ነበር እንዴ?)

#2 -: ” ኢፍትሐዊነት” በስፋት ያለው በራሳቸው በክልሎች ውስጥ ( ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ዞን) እንጂ በክልሎች መካከል አይደለም።

( እኔ: ሚስተር ጄኔራል የኦህዴድ እና ብአዴን ድርጅታዊ መግለጫ አልተመለከቱትም እንዴ? ወይስ አይስማሙበትም?)

#3 -: ኢህአዴግ የፓሊሲ ችግር የለበትም። ችግሩ ማስፈፀም አለመቻል ነው።

( እኔ:- ሚስተር ጄኔራል #3 እና ቀጥሎ የሚፃፈውን #4 ንግግርዎን ለማዛመድ ይሞክሩ።)

#4 -: ትግራይ ውስጥ ግብርና መር ፓሊሲ አይሰራም።

( እኔ:- ሚስተር ጄኔራል ታዲያ ሌላው ምን ተዳው ነው?)

#5 -: ፋብሪካ የተከማቸው አዲስ አበባ ላይ ብቻ ነው። እዚም እዚያም ያለው ፋብሪካ ጥቂት ነው። ዋናው ግን የፋብሪካ መብዛት ሳይሆን የአእምሮ ልማትና የአስተሳሰብ እድገት ነው።

( የጋዜጠኛ አንሙቴ ኢንቴግሪቲ:- አንሙቴ መጀመሪያ ” ሰው እኮ ፋብሪካ እየቆጠረ ነው” በማለት ህዝቡ የአእምሮ ልማት አለማሰቡን አጣጥሎ ሳይጨርስ የተናገረውን ረስቶት ” እኔ ግን ጋንቤላ ውስጥ አንድ ፋብሪካ አለመኖሩ ቅር ያሰኘኛል” ይለናል።

( እኔ:- አንሙቴ ኢንቴግሪቲውን ለጊዜው ትቼው ቅሬታህን ግን እኔም እጋራለሁ። እርግጥ የጋንቤላን መሬት 70 በመቶው የተቀራመቱት የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው ስጨምርበት ደግሞ ቅሬታዬ የትየለሌ ይሆናል።)

#6 :- ተቃዋሚዎች የመከላከያ ሰራዊታችን ጄኔራሎች ትግራይ ነፃ አውጪ ናቸው ይላሉ። አሁንም እንደዛ ያስባሉ። ይሄ ትክክል አይደለም። የመከላከያ ሰራዊታችን በአሁን ሰአት ተመጣጥኗል።

( እኔ:- ሚስተር ጄኔራል እስቲ ጄኔራሎቹን በብሔረሰብና በያዙት የስልጣን ቦታ ዘርዝረው ያቅርቡልን? አደራዎትን የኮማንድ ፓስቱ የህዝብ ግንኙነት ሐላፊ ጄኔራል መሐመድ ፣ ብሔረሰብ አማራ ብለው እንዳያሸማቅቁን! አንሙቴም ቢሆን እዝች ጋር ያሳየሃትን ከኢንተግሪቲ መንሸራተት ሌላ ሰው ሳያያት አርማት)

#7 :- ሕውሓት ጠንካራ ድርጅት ነበር። አሁን ግን እንደዛ አይደለም።

( እኔ: – No comment!)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.