የዶክተር አብይ የብቃት ምዘና ፈተና – በድሬቲዩብ

ዝመተኛው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ግምገማ እንደቀጠለ ነው፡፡ የገዥው ፓርቲ ኮምኒስታዊ ዓመል ጎልቶ የሚሰተዋልበት እንዲህ ያለው ስብሰባ ለብዙ መላምቶች የተጋለጠ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ለዚህም ይመሰላል ሁሉም በየፊናው የቢሆን ዓለሙን ፈጥሮ ስለ ግመገማው እየፃፈ፣ እየዘገበ፣ እያወራ የሚገኘው፡፡

በእንዲህ ያለው የግምት ጨዋታ ውስጥ ሱሰኛ የሆኑ ኃይሎች በየቀኑ ስለ ኢህአዴግ ግምገማ ያሻቸውን ያለከልካይ ይነግሩናል፡፡

ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት እገሌ ጠ/ሚንሰትር ሆኖ ተመርጧል ሲሉን የነበሩ ወገኖች አሁንም ከዚህ አዙሪት መላቀቅ ተስኗቸዋል፡፡

በዚህ የተነሳም የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ግምገማ ከጀመረበት ቀን እንስቶ እስካሁን በየዕለቱ ጠቅላይ ሚንሰትር ይመርጡልናል፡፡

ይህን አሉባልታ ትተን በዝመተኛው ግመገማ ውሰጥ እየቆጠረ ስላለው ስዓት እናውራ፡፡

ስድስት ቀናትን ባሳለፈው የግንባሩ ስራአስፈፃሚ ስብሰባ ፤ እስካሁን ብሄራዊ ድርጅቶች በነበራቸው የተናጠል ግመገማ እራሳቸውን እንዴት አይተው መጡ የሚለው ሃሳብ ሲቀርብ እንደነበር መገመቱ አዳጋች አይደለም፡፡ በኢህአዴግ ቤት እንዲህ ያለው አራቱ ብሔራዊ ድርጅቶች እራሳቸውን ያዩበት መንገድ ቀርቦ ከሌሎች አሰተያየት እንዲቀበሉ የሚደረግበት መንገድ በርካታ ቀናትን ሲወስድ የኖረ ጉዳይ ነው፡፡

የስብሰባ ሱሰኛ የሆኑት አብዛኞቹ አመራሮች በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ዕልህ አስጨራሽ ክርክር እንደሚያደርጉም ይጠበቃል፡፡

የሚገመገመው ብሄራዊ ድርጅት ከቀሩት ድርጅቶች የሚደርሰውን አስተያትም ተቀብሎ በድጋሚ ያስተካክላል፡፡ ይህ የኢህአዴግ አካሄድ በአራቱ እህት ድርጅቶች ውስጥ በቅርቡ የተከናወኑ ግምገማዎች በድጋሚ እንዲታዩም የሚያስገድድ ሊሆንም ይችላል፡፡

በዚህ በኩል በዋነኝነት ኦህዴድ እራሱን የገመገመበት መንገድ በኢህአዴግ ዕህት ድርጅቶች እንዴት ይታይ ይሆን የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ነው? ኦህዴድ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በኢህአዴግ ቤት ያልተጠበቀ አብዮትን የፈጠረ ፓርቲ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም፡፡ ይህ አብዮት ግን አንዳንዴ ህዝቡን ተጠቃሚ ሲያደርግ ሌላ ጊዜ እየጎዳ የተጓዘ ነው፡፡

ከአንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ጋር በቅርብ ስወያይ እንደገለፁልኝ የኦህዴድ ፖለቲካዊ አካሄድ ብልጠት የሚጎለው የልጅ ጨዋታ ዓይነት ነው፡፡ የፖለቲካ ሳይንሱ ምሁሩ ለዚህ ሀሳባቸው መከራከሪያ የሚያደርጉት የኦህዴድ ባለስልጣናት ኢህአዴግ ቤት መጨረስ ያለባቸውን የቤት ስራ ሁሉ ሳይጨርሱ እየወጡ ለህዝብ መናገራቸው ክልሉን ይበልጥ እንዳይረጋጋ ሲያደርገው ቆይቷል፡፡

የእኒህ ሰው ሙግት ኢህአዴግም ቤት እንደሚኖር የሚጠበቅ ነው፡፡ የኢህአዴግ ዕህት ድርጅቶች በአሁኑ ወቅት ኦህዴድን የሚገመግሙበት ዋና ነጥባቸው በግንባር ድርጅቱና በህዝቡ መካከል እንቅፋት ሁነሀል በሚል ሃሳብ የተቃኘ እንደሚሆን አያከራክርም፡፡

የፌደራል መንግስቱ ውሳኔዎችም ሆነ የኢህዴግ ስራ አስፈፃሚ አቅጣጫዎች ከቅርብ አመታት ወዲህ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብዙ ቦታ እያገኙ እንዳልሆነ የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡ በዚህ ምክንያትም የፌደራሉ መንግስት በእኔና በኦሮሞ ህዝብ መካከል ያለው ዋነኛ እንቅፋት ኦህዴድ ነው ብሎ ማመኑ የሚቀር አይመስልም፡፡

በቅርቡ እንኳን የማዕድን ሚንስቴር የኦሮሚያ መንግስት ለስራየ ዕክል እየፈጠረብኝ ነው ሲል አፍ አውጥቶ ተናግሯል፡፡ የኢንቨስትመንት ኮሚሽንም በስንት ውተወታ የመጡ የውጭ ባላሀብቶችን የክልሉ መንግስት ከጎናቸው አልቆመም የሚል ሀሳብ ሲሰነዝር ተሰምቷል ፡፡

የመከላላክያና የፌደራል ፖሊስ ተቋማትም በክልሉ ለተሰጣቸው ሃላፊነት መሰናክል ብለው የሚጠቅሱት ጉዳያቸው የኢህአዴግ ዕህት ድርጅት የሆነውን ኦህዴድን እንደሚሆን መገመቱ ስህተት አይመስልም፡፡

በዚህ ስዓት ኢህአዴግ ቤት ኦህዴድ የማይወደድለት ሌላው ጉዳይ ደግሞ ካለበቂ ምክንያት የአመራር ለውጥ ማድረጉ ነው፡፡ አቶ ለማን አውርዶ ዶ/ር አብይን ሊቀመንበር ያደረገው ኦህዴድ ከአንድ መሰረታዊ የገዥው ፓርቲ አሰራር ጋር መጋፈጡ አይቀሬ ነው፡፡ ኢህአዴግ ቤት ሁሉም የዕህት ድርጅት አባላት እኩል ናቸው የሚል መርህ አለ፡፡

ይህ መርህ በአንድ የፓርቲ ፕሮግራም እስከተዳደርን ድረስ ከየትኛውም ብሄራዊ ድረጅት ሊቀመንበር ቢመረጥ ትልቅ ጉዳይ አይደለም የሚል መልዕክት አለው፡፡ ኦህዴድ ሰሞነኛ ስሀተቱ ከዚህ ይመነጫል፡፡ አንድ አምሳል አንድ አካል ነኝ ብሎ የመሰረተውን ኢህአዴግን እኔ ካልመራሁ የሚመስል እንድምታ ያለው ያልታሰበ የአመራር ለውጥን አድርጓል፡፡

ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባላት ይህ ተግባር በቀላሉ የሚዋጥላቸው እንደማይሆን ይገመታል፡፡ እንዲህ መሆኑ ደግሞ ኦህዴድ ቤት የተሰራውን የፖለቲካ ቁማር ሊያከሽፈው ይችላል፡፡ የፓርላማ አባል የሆኑትን ዶ/ር አብይን ወደ ሊቀመንበርነት በማምጣት ለጠቅላይ ሚንስትርነቱ ሳይቀር ለመፋለም የወሰነው ኦህዴድ በራሱ አዙሪት የተበተበ ይመስላል፡፡

ይኼ ደገሞ የዶ/ር አብይን ቀጣይ ጠቅላይ ሚንሰትር የመሆን ዕድል ያመነምነዋል፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉትም ዶ/ር አብይ በኢአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ሊቀመንበር የሚሆኑበትን ዕድል ብቻ ሳይሆን ዕጩ የሚሆኑበትንም ዕድል ያጠብባቸዋል፡፡ ኢህአዴግ ሊቀመንበሩን ከመምረጡ በፊት እያንዳንዱ ዕጩ ቢያንስ 60 ያህል ድጋፍ ከቤቱ ማግኘት ይኖርበታል፡፡

ቀመሩ ሲተነተን የኦህዴድ አባላት ሙሉ በሙሉ ዶ/ር አብይን ቢደግፉ እንኳን 15 ተጨማሪ ድምፆችን ከሌሎች ድርጅቶች የማግኘት ግዴታ ይጥልባቸዋል፡፡ ይህ እንግዲህ ዕጩ ለመሆን ብቻ የሚያስፈልግ መስፈርት ነው፡፡ ኦህዴድ የሊቀመንበርነቱን ቦታ ለመያዝ የሚያደርገው ጉዞ አጣብቂኝ ውስጥ መግባት የሚጀመረውም በዚህ ገዥው ፓርቲ ውስጥ ባለ የብቃት ምዘና ፈተና የተነሳ ነው፡፡

ኢህአዴግ ቤት ያለውን የኦህዴድ ግምገማ ያዩ አባላት በድፍረት በሊቀመንበርነት ዕጩነቱ ላይ ከኦህዴድ ጎን መቆም ይችላሉ ወይ?

ከቆሙስ ነገ በራሳቸው ብሄራዊ ድርጅት ላለመገምገማቸው ዋስትናቸው ምንድን ነው? ምለሹ ፈተናው ለዶ/ር አብይ ብቻም ሳይሆን ለፓርቲውም ጭምር እንደሚሆን ይጠቁመናል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.