ስለ እኔ ስለ እነርሱ! – ሀብታሙ ኪታባ

1. ስለ እኔ
የኢትዮጵያን አንድነትን ለማጠናከር፣ የህዝብ የሆነ መንግሥት እንዲኖር፣ የሚታመኑ የዲሞክራሲ ተቋማት እንዲኖሩ፣ ዜጎች በዘራቸው ሆነው በሚከተሉት ፖለቲካዊ አተያይ የማይለያዩበት ቀን እንዲመጣ፣ ሚዲያዎች ከእስራት እንዲፈቱ፣ እና ኢትዮጵያ ከስልታዊ ዘራፊ መፍያዎች (ኮንትሮባንዲስቶቹን ይጨምራል) እንድትላቀቅ … ለመጻፍ፣ ለመናገር፣ ለመስራት የማንም አካል ይሁንታ ሆነ በጎ ፈቃድ አያስፈልገኝም፡፡ አየርን ወደ ውስጤ ለመሳብ የማንንም ፈቃድ እንደማልጠይቀው ለእዚህም እንዲሁ ነው የማስበው፡፡

አንዳንድ ወዳጆቼ በውስጥ መስመር እንዲሁም በስልክ ለእኔ በመስጋት ምክራቸውን ይሰጡኛል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ በሙሉ አመሰግናለሁ፡፡

እግዚአብሔርን አላሳዝን እንዲሁም ህግን አልተላለፍ (አንዳንድ የማላምንባቸውን ህጎችን ጨምሮ) እንጂ የምይዘው አቋም የሚያስከፋቸውን ግለሰቦች ሆነ ፓርቲዎች አስቤ የምቀይረው አይደለም፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ከመጻፍ ባሻገር የምሰራውም

በተደጋጋሚ እንዳልኩት የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል አይደለሁም; የየትኛው ፖለታካዊ ፖርቲ ርዕዩት አለም ተከታይም አይደለሁም፣ ለየትኛውም ጎሳ የተለየ ራዕይ የለኝም …!!!

የምይዛቸው አቋሞች ሆነ የማራምዳቸው ሃሳቦች ምንጫቸው ከፖለቲካዊ ርዕዮት አለም መለስ ባለ የፍትህ እና የኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ለተወሰኑ ሰዎች ወይንም ቡድኖች ሳይሆን የሁሉም ዜጎች የሆነች ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡

2. ስለ እነርሱ
ከሁለት አጽናፍ ወግናችሁ የምትታኮሱ የፌስቡክ አርበኞች ለሁላችሁ ምክር አለኝ የራሳችሁን አቋም ፍጹም ትክክል በተቃራኒ ያደረጋችሁትን አቋም ፍጹም ስህተት አድርጋችሁ የምታከናውኑት ትግል ለኢትዮጵያ አዲስ/ተረኛ አምባገነን ያመጣ ይሆናል እንጂ ለኢትዮጵያ የሚፈይደው የለም፡፡ ኢትዮጵያ የሚያሻት አንድ extreme በሌላ extreme መተካት ሳይሆን በህዝቡ ዘንድ ተአማኒነት ያላቸው የዲሞክራሲና የመንግሥት ተቋማትን መመስረት ነው፡፡ ይህ በሆነ ጊዜ የተጻፈው ህግ መታመን ቻለ ማለት ነው፡፡ የተጻፈው ህግ በታማኝነት ከተፈጸመ የሚቀረው ስራ ለህዝብ የሚበጀውን ህግ ማድረግ የማይበጀውን ማስወገድ ነው፡፡

የኢህአዴግ ውድቀት መነሻው ከሌሎች የቀድሞ መንግሥታት በከፋ ሁኔታ የመንግሥት ተቋማት እንዳይታመኑ መሆናቸው ነው፡፡

• የማይታመን ምርጫ ቦርድ፣
• የማይታመን ደህንነት (ኢትዮጵያን ሳይሆን ኢህአዴግን የሚጠበቅ)፣
• የማይታመኑ ሚዲያዎች፣
• የማይታመን የህግ ስርአት፣
• የማይታመን ጸረ-ሙስና፣
• የማይታመን እምባ ጠባቂ፣
• …???????????

ለማይታመኑ ተቋማት የግብር ከፋዩ ገንዘብ ይመደባል፡፡ የማይታመን ስራ እንደሚሰሩ የሚያርቡ የእኒህ ተቋማት ሰራተኞች በየፌርማታው “አብዮታዊ ዲሞክራሲን” ያለ ፍላጎታቸው ይጋታሉ፣ እያጉረመረሙ ሰልፍ ይወጣሉ፣ ለለውጥ ሳይሆን ለመኖር በመኖር ሃሞት በጀት አመቱን ይገፋሉ::

መፍትሔው ግልጽ ቢሆንም አራት ለኢትዮጵያ የሚበጃትን የመፍትሔ ሃሳብ እንደሚከተለው ዘርዝሬአለሁ፡፡ ችግሩ እኒህ ነገሮችን በኢህአዴግ ዘንድ አለመታወቃቸው አይደለም፡፡ ችግሩ የጥቅመኛ ግለሰቦችና ቡድኖች ከህግ በላይ መሆን ነው፣ ችግሩ የሁለት extreme እልህ ነው፣ ችግሩ ጎመን በጤና ብሎ ዝምታን የፈጠረው ህዝብ የልብልብ የሚሰማቸው “ስህተትን ትክክል” እንደሆነ እንዲያስቡ የሆኑ የፖለቲካ ዘዋሪዎችን መፍጠሩ ነው …

የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ፍትህና ህግ የበላይ የሆነበት አገር ለመመልከት የሚሰራው ስራ ፍሬ ማፍራቱ አይቀሬ ነው፡፡ ለሁሉም የሚሻለው ይህ ነውና፡፡ እውነት ወይንም ትክክል መሆን መቼም የሚያዋጣ ነውና፡፡

እነሆ መፍትሔ ለኢትዮጵያ፡-

መፍትሔው፡-
  1. ተአማኒ ተቋማትን መፍጠር
  2. ለህግ መገዛት
  3. አላስፈላጊ ህጎችን መሻር
  4. አስፈላጊ ህጎችን መደንገግ

ምንጭ ፌስቡክ: ሀብታሙ ኪታባ ገፅ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.