የሌለው ማን ነው? – ልሳነ አማራ

አማራነትን…..በወልቃይት ጸገዴ፣ በአርማጭሆ፣ በጎንደር፣ በደብረ ታቦር፣ በየጁ፣ በአምባሰል፣ በወሎ፣ በይፋት፣ በአንኮበር፣ በመንዝ፣ በመርሀቤቴ፣ በጅሩ፣ በምንጃር፣ … በጎጃም፣ በዳሞት፣ በባሕር ዳር፣ … እየፈለጉት ቢሆንም ገና አላገኑትም፡፡(ፕሮፊሰር መስፍን)

አማራ የሚባል ብሄር አለ ተብሎ የራሱ አስተዳደር ከተሰጠው እብድነት ነው፡፡ አማራ የሚባል ብሄር ኢትዩጲያ ውስጥ የለም፡፡፡ለሌለ ነገር ውክልና አያስፈልግም …ፕሮፊሰር መስፍን ወልደማርያም በ1980 ዎቹ መጀመሪያ ክልል ለማዋቀር ሲባል ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ የተናገሩት፡፡

ቴዎድሮስ የሚባለው ተራ ሽፍታ ነው፡፡ በመጨረሻም ሰው ሁሉ በጭካኔው ትቶት ብቻውን ሞተ( ፕሮፊሰር መስፍን 2009 ኣም)

በላይ የጎጃም ሰው ሳይሆን አሮሞ ነው(ፕሮፊሰር መስፍን 2009)

ከመምህር ገብረኪዳን ደስታ (የትግራይ ህዝብ እና የትምክህተኞች ሴራ ከትናንት እስከ ዛሬ) አስከ ተስፋየ ገብረአብ (የቡርቃ ዝምታ) አማራውን በጠላትነት ፈርጀው ጽፈው ስብከታቸውን ለሩብ ክፍለ ዘመን ዘለቁ፡፡ ይዝለቁ (ብሄርተኝነቱ ዘለቄታቸውን አቁሞታል)

አማራነትን አውግዞ ኢትዮጲያዊነትንም አሳንሶ የተነሳው የ1960 የብሄር ማርክሳዊ የሌኒን ፖለቲካ በአማራው ጨቋንነት ላይ ፤በሌሎች ብሄሮች ተጨቋንነት ላይ ተሰመረ፡፡

ስለዚህ አማራው እንደ ገዥ መደብ ሌሎች ብሄሮች ከጭቆና ነጹ ይባሉ ዘንድ መኖር ነበረበት፡፡ አማራው ከሌለ የዘውጌ ብሄርተኝነት አይፋፋምም ነበር፡፡

የላችሁም ይሉናል፡፡ሲያሳድዱን እና ሲገሉን ግን ያገኙናል እንዳሉት ፕሮፊሰር አስራት አማራው ህልውናውን ለመጠበቅ ራሱን ሲወድ የለም ፤ዘረኛ …ምናምን የሚሉ ትችቶች ይወረወራሉ፡፡ዳሩ ተወርውረው አያልሙም፡፡

ፕሮፊሰር መስፍን እንኳን ካፈርኩ አይመልሰኝ ብለው እንጂ የአማራን ደማቅ ታሪክ ህሌናቸው ይክደዋል ብየ አላስብም፡፡( ህሌናቸው ይሄን ሃቅ ከካደው እሳቸው በህይዎት የሉም ማለት ነው፡፡ከሌለ ሰው ጋር ደግሞ መከራከር አይጠቅምም)፡፡ታሪክ መጥቀስ ሳያስፈልግ እኔ አማራ ነኝ የሚል ትውልድ ከፊታቸው ቁሞ እያለ በደካማ አርቲክል የለህም ብሎ መከራከር ከፍ ያለ ዝለት ነው፡፡

ወልቃይት አማራ ነኝ የሚል ጠፋ አሉ፡፡( እነ ኮሌኔል ደመቀ እንዳይሰሙ ብየ አሰብኩ)፡፡ሸዋም አማራ ነኝ የሚል የለም አሉ( ፕሮፊሰር አስራትን አሳሰብናቸው)፡፡ወሎም የለም አሉ( እነብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ጠቀስንላቸው)፡ጎጃምም የለም አሉ(እነየሻንበል ከበደን በምናብ አቀረብኩላቸው፡፡)

እንግዲህ ለወቅቱ ለአማራነት ምልክት የሚሆኑ ሰዎችን አቅርበን አማራ ነን እያሏቸው …. አማራ የለም…. ካሉ ፕሮፊሰር መስፍን ወልደማርያም የሉም ማለት ነው፡፡(እኛ ግን እንዲኖሩን እንፈልጋለን፡፡ብርቱ ሊቅም ናቸው፡፡ሊቅነታቸው ግን ስለ አማራ ያላቸውን አረዳድ አይጨምርም፡፡)

›››

በአማራ ሽማግሌ እና ሊቅ ይከበራል፡፡ ፕሮፊሰር መስፍንም እናከብራቸዋለን፡፡እሳቸው አማራ የለም ሲሉ ምናልባት አማራነት ላልፈለጉት እየቆየ የሚገባ ሳይንስም ሆኖባቸው ሊሆን ይችላል፡፡(ይሄን የሚረዱበት ተጨማሪ ዕድሜ እንዲሰጣቸው አንድየ፤ ለዲያቆን ፕሮፊሰር መስፍን መልካም ምኞታችን ነው፡፡)

…..

ፈረንሳይ በ 19 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት የለችም፡፡ ዩክሬን እና ሌሎች የታላቋ ሩሲያ 14 ግዛቶች ከ1992 በፊት የሉም፡፡ የሉም ማለት አንድ ዩክሬናዊ ጃፓናዊ ነው ማለት አይደለም፡፡ዩክሬናዊው ራሱን በሩሲያዊነት ይገልጻል ማለት እንጂ፡፡ ፈረንሳይም ጦረኛው ናፖሊዮን ቦናፓርቲ ብሄርተኝነቷን ከመስራቱ በፊት ፈረንሳያዊ ነኝ የሚል ዜጋ ብዙ አልነበራትም፡፡በዛን ወቅት የነበረው ፈረንሳያዊ ግን ሱዳናዊ ሆኖ አይደለም፡፡ወቅት እና ፖለቲካ ተነባብረው የሰውን እኔነት ይገልጣሉ፡፡ አስከ 1847 ኢትዮጲያ በብዛት አብሲኒያ ስለምትባል ኢትዩጲያዊ በብዛት ራሱን በአብሲኒያዊ ብሎ ይገልጻል… ግን .በዛን ወቅት ኢትዩጲያዊ አለ፡፡ነገም ኢትዩጲያ ኩሽ ብትባል ኢትዮጲያዊ የለም ማለት አይቻልም እኮ፡፡

….

ከ1966 በፊት አሮሞነት በዛሬው ስያሜ እና ቅርጽ አልነበረም፡፡የኦነግ እንቅስቃሴ ግን የሜጫ እና ቱለማን ማህበር ኦሮሞኛ ተናጋሪ ህዝቦችን ባንድ ላይ አካቶ አሮሞ በሚል መጠሪያ ብሄርተኝነቱን አጎነው፡፡ይህ ማለት ግን ከ1966 በፊት ወለጋ አሮም አይደለም ማለት አይደለም፡፡የሌሎች የሀገራችን ብሄሮችም ተመሳሳይ ነው፡፡

….

በቀላል አቀራረብ ፕሮፊሰር መስፍን አሮሞኛ ብለን አሮሞን፣ጉራጌኛ ብለን ጉራጌን፣ እንግሊዝ ብለን እንግሊዘኛ ካልን አማርኛ ብለን ማን እንበል ሲባሉ በእብሪት ዘለው ኢትዮጲያ ይላሉ፡፡(ቋንቋ ማህበረሰብ ያሥፈልገዋል፡፡ ማህበረሰብ አልባ ቋንቋ የለም፡፡አማርኛ ከመንግስተ ሰማያት ለጻድቃን የወረደ ቋንቋ አይደለም፡፡በአማራዎች የተፈጠረ ልሳን ነው፡፡)

..

በመካከለኛው ዘመን የግብጽ ከሊፎች ለኢትዮጲያ ነገስታት የጻፏቸው ጦማሮች ንጉሰ አማራ ይላሉ…ይሄን በደብረ ሊባኖስ እና በአማራ ሳይንት በተድባበ ማርያም ጥንታዊ የብራና ጹሁፎችን መመርመር ይቻላል)፡፡መቼም የቅርቡ በ1262 አካባቢ ንጉሰ አምሃራ ብሎ የነገሰው ይኮኖአምላክ ለወንበሩ አይደለም፡፡ ለህዝቡ ነው፡፡ ያም አማራ ለተባለ ህዝብ….the medival history of Ethiopia seregew (phd)

….

አማራነት በኢትዮጲያ የምስረታ ታሪክ ውስጥ የጎላ አበርክቶ ስለነበረው ኢትዩጲያዊነትን እንደ ራሱ ተመልክቶ ራሱን በዜግነቱ ገልጻል፡፡ እንግሊዛውያን እንደ ዌልስ እንደ አየርላንድ እንደ እሶኮትላንድ ለሀገራቸው ለታላቋ ብሪታኒያ ወይም ለተባበረችው እንግለዝ (united kingdom)እንጂ ለእንግሊዝ እንደ ብሄር አያስቡም፡፡ብሄራቸውን በዜግነት ማንነት ውስጥ አቅልመውታል፡፡ አማራም የራሱን ማንነት በኢትዩጲያዊነት ውስጥ ስለማያጣው ስለ አማራነቱ መተርክ አስገዳጅ ሁኔታ አላጋጠመውም ነበር፡፡(ልክ ራሻያዎች ስለ ታላቋ ሩሲያ እንጂ ስለ ራሽያ ብሄር እንደማይጨነቁት፡፡)

….

መሰረትን በመናድ ላይ የተመሰረተው የ 1966 ፖለቲካ ኢትዩጲያዊን የብሄር መዋጮ አደረጋት፡፡አማራው ከሀገሪቱ ባለአክስዮን ይሆን ዘንድ እንደ ብሄር መደራጀት ያስፈልገዋል ሲባል ፕሮፊሰር መስፍን የለም፡፡የሌለ አይደራጅም ሲሉ በርትተው ተከራከሩ፡፡አስከ 1984 መአህድ እስከሚመጣ አማራው ዳር ተቀመጠ፡፡ ዳር ተቀምጦም ግን አላመለጠም፡፡ ተፈናቀለ፡፡ኢትዮጲያዊነት ለብቻው አዳኝ እንዳልሆነ ስላመነ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት ተብሎ በፕሮፊሰር አስራት መሪነት ተደራጀ፡፡በወቅቱ ፕሮፊሰር አስራትን ፕሮፊሰር መስፍን ዘረኛ ምናምን ብለው ወቀሷቸው፡፡ፕሮፊሰር መስፍን አማራ ላይ አመክንዮ ሳይሆን እልህ አለባቸው፡፡ብሄሩ ባይኖርም እኮ ተደራጅቶ መብትን ማስከበር የጤነኞች ሳይንስ ነው፡፡ግን አልደገፉም፡፡ ፕሮፊሰር መስፍን የጠሉት መአህድ በፈጠረው እርሾ በ1997 ቀስተዳመናን ወክለው ከቅንጅት ጋር ግን ሰርተዋል፡፡( መአህድ ከ 1992 በኋላ ወጣቱ ክፍል በነ ልደቱ እና አንዷለም አራጌ ኢዴፓ ሌላው ደግሞ መኢአድ ሆኖ በነኢንጅነር ሃይሉ ሻውል ቅንጅትን ፈጥሮ የምርጫ 97 ን ተውኗል፡፡የቅንጅት መሰረት ፕሮፊሰር መስፍን የሚተቹት መአህድ ነው፡፡መአህድ ፕሮፊሰር አስራት ነው፡፡)

አማራነትን በመናድ የሚገነባ የኢትዮጲያ አንድነት አይኖርም፡፡ አማራነትም ከኢትዮጲያዊነት ጋር ቅራኔ የለውም፡፡

…..

ለዚህ ሁሉ ትችት መልስ የሚሰጠው የአማራ ብሄርተኝነት ይሆናል፡፡የአማራ ብሄርተኝነት ማንንም ጠልቶ እና በጠላትነት ፈርጆ የቆመ የቂም በቀል ብሄርተኝነት አይደለም ና ፕሮፊሰሩን እና መሰሎቹን የብሄርተኝነቱ አካል ቢሆኑ ታሪክ ይክሳቸው ነበር፡፡


የሺ ሃሳብ አበራ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.