የተጀመረውን የሰላም ውይይት ለማሳካት በኦሮሞ ነጻነት ግንባር የታወጀ ግዜያዊ የተኩስ ማቆም መግለጫ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን የፖለቲካ ችግር ለመፍታት በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲበጅለት ለረጅም ዓመታት በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርብ እንደነበር ይታወቃል። ሰሞኑንም እንዲሁ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርብ ነበር። ይሁን እንጂ ለረጅም ዓመታት በኦነግ ሲቀርብ የነበረው የሰላም ጥሪ ምላሽ ሳያገኝ ቆይቷል።

በቅርቡ ግን በሊቀ-መንበሩ በሚመራው የኦነግ የልዑካን ቡድንና በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ኣብይ ኣህመድ መካከል በተደረገ ንግግር፡ ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሲደረግ የነበረው ጥረት ኣንድ እርምጃ ወደፊት ሊሄድ የቻለ መሆኑን ኦነግ ያምናል። ኦነግ ይህን የተጀመረውን የሰላም ንግግር መንግስታት፣ ህዝቦችና ሰላም-ወዳዶች የሚሹት መሆኑንም ይገነዘባል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይህንን በመረዳት የተጀመረውን የሰላም ንግግር ከደረሰበት ወደፊት ለማራመድና ለማሳካት ይረዳል በሚል እምነት፡ የሚሰማራብንን የመንግስት ሃይል ከመከላከል በተረፈ ለጊዜው ተኩስ ማቆሙን ያውጃል። ለጊዜው ይህ የተኩስ ማቆም ኣዋጅም የተጀመረው ንግግር የሚጠበቀውን ፍሬ ኣግኝቶ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርና የኢትዮጵያ መንግስት በጋራ ኣጠቃላይ ጦርነት የማቆም ኣዋጅ ያውጃሉ የሚል እምነት ኣለው።

ስለሆነም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ይህንን የተላለፈውን ጊዜያዊ የተኩስ ማቆም ኣዋጅ በመገንዘብ በያለበት ቦታ ሁሉ ስራ ላይ እንዲያውል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስራ-ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ይህን መመሪያ ያስተላልፋል።

ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው !

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!

ሓምሌ 12, 2018ዓም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.