የፊንፊኔ ከንቲባ ኦሮሞ መሆኑ የጦዘ ክርክር ማንሳቱ እያየን ነው። ክርክሩ የተጠበቀ ቢሆንም የመከራከሪያ ነጥቦቹ ትንሽ ገርመውኛል።

የኦሮሞ ህዝብ ከከተማዋ ያለው ጉዳይ ከንቲባ ከኛ ይሁን የሚል አይደለም።

እንደዚያማ ቢሆን እኮ ኢሀአዴግ ከገባ ጀምሮ ከ አርከበ በስተቀረ ሁሉም ከንቲባዎች ኦሮሞዎች ነበሩ አይደል እንዴ? ታዲያ በነዚያ ከንቲባዎች ስር ኦሮሞ ተጠቀመ ወይስ ተጎዳ? መልሱ ቀላል ነው። በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የኦሮሞ አባወራ ገባሬ መሬቱን ተነጥቆ የተፈናቀለው እኮ ከንቲባዎቹ ኦሮሞ ሆነው ሳለ ነው። የኦሮሞ ወጣቶች በአዲሱ ከንቲባ ታከለ ኡማ መሾም የተደሰቱት ኦሮሞ ስለሆነ አይደለም። ልጁ በከተማዋ መስፋፍት ምክንያት በተነሳው የማስተር ፕላን ቁጣ ፈር ቀዳጅ ተቃውሞ በማሰማት የትግሉ ክብሪት ከመሆኑ አንጻር ቢያንስ ቢያንስ እንደ ከንቲባ የገበሬውን መፈናቀል ያስቆማል በሚል ተስፋ ነው። ከዛ በተረፈ ኦሮሞ እና ኦሮሚያ በከተማዋ ላይ ያላቸውን ህገመንግስታዊ መብት ከንቲባው ማንም ሆነ ማን ሊፈታ ይችላል የሚል እምነት የለም። ያንን ጉዳይ መፍታት ያለባቸው የኦሮሚያ፣ የፌደራል እና የከተማዋ አስተዳደር በሚያደርጉ ድርድር ነው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ አንድ ቀልብ የሚስብ ክርክር እየተካሄደ ነው። ይህም ከተማዋ መተዳደር ያለባት እዚያው ሸገር በተወለደ ሰው ነው ይላል ( ሰገጤ ሳይሆን ሸነግ ይግዛን ነው ያላችሁት? lol) የሚገርመው ደግሞ ይህን የመከራከሪያ ነጥብ የሚያነሱት ወትሮ ‘አንድ ሰው የትም አከባቢ ከማንም ብሄር ቢወለድም የትኛውንም የኢትዮጲያ ክፍል የመኖር፣ የመስራት እና የማስተዳደር መብት አለው’ የሚሉ ናቸው። እናም አሁን ሸገርን በሸገር ልጆች ብቻ የሚለው ክርክር ከቋሚ መከራከሪያቸው ይጣረሳል። እኔ የተሻለ ብዬ ያገኘሁት መከራከሪያ ከተማዋ እነደማንኛውም አከባቢ በህዝብ በተመረጡ ሰዎች ትትዳደር የሚለው ነው። ይህንን ሀሳብ የሚያነሱትም ቢሆኑ ስለ ምርጫ በተነሳ ቁጥር አሁን ምርጫ አያስፈልግም የለውጡን ንፋስ enjoy እናድርግበት: ዘና ብለን እንደመርበት አትረብሹን የሚሉ መሆናቸውም የሚገርም ነው። አዲሱ የለውጥ አመራር ተመችቶናል ያለምንም ምርጫ አንድ አምስት አስር አመታት ይሰጠው ብለው ሲከራከሩ ከርመው አሁን ያው አዲሱ የለውጥ አመራር የሾመውን ከንቲባ በመቃውም በምርጫ መሆን አለበት ማለት ያስኬዳልን?

ላማንኛውም ክርክራችን አያልቅም። ሊያልቅም አይገባም።ላለፉት አመታት አየር ባየር በሶሻል ሚዲያ ስናጦዛቸው የነበሩትን ክርክሮች አሁን መሬት ላይ አውርደን ተቋማዊ አካሄድን ተከትለን በዩኒቨርሲቲዎቻችን ውስጥ ወደ ማካሄድ መሸጋገር አለብን። I am looking forward to debating and discussing at our univiersity halls?. How about you?

መልካም ይስራ ዘመን ለ ኢ/ር ታከለ ኡማ እና ካቢኔያቸው!

Advertisements