ኦሮሞ እና አማራ ለኢትዮጵያ ትልልቅ መሰረቶች ናቸው። – ጃዋር ሙሃመድ

የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር ሙሀመድ እና ሌሎች አክቲቪስቶች ባሕር ዳር ገቡ፡፡

‹‹ እኔ የመጣሁት የአማራ እና የኦሮሞን ህዝብ ተፈጥሯዊ ትስስር ለማጠናከር ነው፡፡ ኦሮሞ እና አማራ ለኢትዮጵያ ትልልቅ መሰረቶች ናቸው።›› ጃዋር ሙሃመድ

በባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በአቀባበሉ የተገኙት የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ‹‹ኦኤምኤን በአማራ ክልል ያለውን ልማትና ዴሞክራሲ ለማስፈንና ለውጡን ለማጠናከር አጋር ነው፤ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እና ከክልሉ ህዝብ ጋርም በጋራ ይሰራል›› ብለዋል፡፡

ጃዋር ሙሀመድ በአቀባበል ስነ-ሰርዓቱ እንደተናገረው በአሁኑ ወቅት ላለው ለውጥ የአማራ ህዝብና መንግስት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ‹‹የአማራ እና የኦሮሞን ህዝብ ተፈጥሯዊ ትስስር ለማጠናከር ነው የመጣሁት›› ነው ያለው አቶ ጃዋር፡፡ ‹‹የሁለቱን ህዝቦች ትስስር ለማጠናከር የምችለውን አደርጋለሁም›› ብሏል፡፡

አቶ ጃዋር ሙሀመድ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


ምንጭ: አብመድ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.