ኦዴፓ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ – ኢዜአ

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ባለ9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ምርጫ የኦዴግ/ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።

በጅማ ከተማ በተካሄደ ባለው የፓርቲው 9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ነው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫው በዛሬው እለት የተካሄደው።

በዚህም መሰረት፦

1. ዶክተር አብይ አህመድ

2. አቶ ለማ መገርሳ

3. ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ

4. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ

5. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

6. አቶ አዲሱ አረጋ

7. አቶ ሽመልስ አብዲሳ

8. አቶ ፍቃዱ ተሰማ

9. ዶክተር ዓለሙ ስሜ

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ተመርጠዋል።

9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔም ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ዶክተር አብይ አህመድ የተለያዩ ውሳኔዎች የተላለፉበት ይህ ድርጅታዊ ጉባኤ ታሪካዊ ነበር ብለዋል።

በተለይም አዳዲስ አመራሮች ወደ ፊት የመጡበት፣ የስያሜ፣ የአርማ እና መዝሙር ለውጥ የተካሄደበት መሆኑ ታሪካዊ ያደርገዋል ነው ያሉት።

ሊቀመንበሩ የኦሮሞ ዴሞራሲያዊ ፓርቲ ህዝቡን ለማገልገል ከዛሬ ጀምሮ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ቃል ይግባልም ብለዋል።

በአዲስ መንፈስና ሀሳብ ለማገልገል የተነሳው ፓርቲው በፍቅርና በአንድነት ለማገልገልም ተግቶ እንደሚሰራም አስታውቀዋል ሲል የዘገበው ኤፍቢሲ ነው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.