ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተፃፈ ግልፅ ደብዳቤ – ከአዲስ አበባ ወጣቶች ህብረት

ክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፤ ገና በጠዋቱ ሃሳብዎትን ደግፎ ከጎንዎ የተሰለፈው፤ ለእርስዎ የታላቋ ኢትዮጵያ ራእይ መሳካት ከጎንዎ በቦምብ ደሙን ያፈሰሰው ወጣት በእስር እና እንግልት እየተዋከበ ነው።

መረጃው እንደሚኖርዎ ተስፋ አለን፤ የኦነግን አቀባበል ምክንያት ሆኖ ከማግስቱ ጀምሮ በቡራዩ በደረሰው ጥቃት ወገንተኝነቱን ለማሳየት ጥቃቱን በመቃወም በጨዋነት ድምፁን ያሰማውን ወጣት በአደባባይ በጥይት ሲገደል፤ ከክቡርነትዎ ምንም አልሰማንም፤ አሁን ደግሞ እርዳታ አሰባስበው በቡራዩ ጥቃት የተፈናቀሉ ወገኖቻቸውን ለመርዳት የሚጥሩ ወጣቶች ሳይቀር በየቦታው እየታሰሩ ይገኛሉ።

ክቡርነትዎ ሃሳብዎን ደግፈን ከጎንዎ የቆምነው በእርስዎ ተስፋ ስላሳደርንና እምነት ስላለን ነውና በፈጠራ ወሬ 60 የኦሮሞ ልጆች ስለሞቱ የቡራዩ ጥቃት ማካካሻ እንደሆነ የሚናገሩ ግለሰቦች በነፃነት እየኖሩ፤ ወገኑን በመርዳት መልካምነቱን እያጎለበተ ለእርስዎም ይሁን ለአዲሱ መንግስትዎ ድጋፉን እያሳየ ያለውን ንፁሁን ወጣት ማሰር ይብቃ እንዲሉ እንማፀናለን።

እኛ የአዲስ አበባ ወጣቶች እንደሆንን ክቡርነትዎ የሰጡንን ተስፋ ዳር ሳያደርሱ፤ ተባብረን ትልቋን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ሳንገነባ፤ ቃልዎትን እውን ሳያደርጉልን አንለቅዎትም፤ አሁንም ወደፊትም እየታሰርንና ውክቢያ እየደረሰብን እንኳን ድጋፋችን አይለይዎትም።

ክቡርነትዎ፤ በአዲስ አበባ የኦነግ አቀባበል ላይ የተነሳው አለመግባባት፤ መንገድና አደባባይን በኦነግ ባንዲራ በመቀባት የሁላችን መጠቀሚያ የሆኑ ነገሮችን በቀለም በማቅለም እና፤ የምኒልክን ሃውልት እናፈርሳለን ባሉ በውሸት ታሪክ የሚመሩ አንድ አንድ የኦሮሞ ወጣቶች ምክንያት እንጂ የአዲስ አበባ ወጣቶች መስቀል አደባባይ ላደሩ የኦሮሞ ወገኖቻችን እራት ሲያበላ ውሃ ሲያቀብል ብርዱን ተካፍሏቸው ነው ያደረው።

መንግስትዎ በእያንዳንዱ ጉዳይ ወጥቶ መግለጫና ማብራሪያ ባይሰጥም፤ ዝምታ በማይገባቸው ጉዳዮች ዝምታን መምረጡ ግን ህብረተሰባችን በአንድነት የአላማዎ ደጋፊ እና አጋዥ እንዳይሆን ግራ እንዲጋባ እና ለአንዳንዶች ክፉ ሃሳብ ማራመጃ እንዲሆን እያደረገው ስለሆነ አፅንኦት እንዲሰጡት እንጠይቃለን።

ክቡርነትዎ፤ ድጋፋችን አይለዮትም።

ከሰላምታ ጋር

የአዲስ አበባ ወጣቶች ህብረት

መስከረም 12 ቀን 2011ዓም

#ጠቅላይ_ሚንስትር_አብይ_አህመድ

#Dr_Abiy_ahemed

#Ethiopia

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.