በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች የታሰሩት የንቅናቄያችን አባላት ብቻ ሳይሆኑ የሌሎች ድርጅቶች አባላትና ደጋፊዎችም ጭምር እንደታሰሩም ተረድተናል – ነአምን ዘለቀ

በአለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ዙሪያ ፣ በቡራዩና ሌሎች አካባቢዎች ነዋሪ በሆኑ በኢትዮጵያ ዜጎች ላይ የተፈጸሙትን አረመኔዊ ግድያዎችና ወንጀሎች ፣ ተያይዞም ከአካባቢው የበርካታ ዜጎቻችን መፈናቀል ተከተሎ በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ታስርዋል። ከተሰሩትም ውስጥ የንቅናቄያችን የአዲስ አበባ የአቀባበል ኮሚቴ አባል የሆነው ብርሃኑ ተክለ ያሬድና ሌሎች የንቅናቄው አባላት መታሰራቸው ይታወቃል። ቅን አሳቢና በአሁን ወቅት በስጋት ላይ የምትገኙ ፣ ምን እየተደረገ ነው? የሚል ጥያቄ በማንሳት ላይ የምትገኙ ወገኖች፣ በአለም ዙሪያም ሆነ በአገር ውስጥ ለምትገኙ አባላትና ደጋፊዎች ሁሉ ብርሃኑ ተክለ ያሬድንና ሰሞኑን የታሰሩትን የንቅናቂያችን አባላትና ደጋፊዎች ለማረጋገጥ የምፈልገው ንቅናቄው ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት ከከፍተኛ የመንግስት የደህነት ሃላፊዎች ጋር በጉዳዩ ላይ በአካል ተነገናኝቶ ተነጋግሮል።

ከዚያም በኋላ ከእነዚሁ የመንግስት አካላት ጋር በመገናኘት የቅርብ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል። ጉዳዩ በህግ ሂደት የሚታይ ነው ስለተባለም ጠበቃ አቁሞአል። በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች የታሰሩት የንቅናቄያችን አባላት ብቻ ሳይሆኑ የሌሎች ድርጅቶች አባላትና ደጋፊዎችም ጭምር እንደታሰሩም ተረድተናል። በእየለቱ የሚመጡትን መረጃዎች ሁሉ ለመሰብሰብና ለማጣራት እየተሰራበት ይገኛል።’ ይህን አንገብጋቢ የሆነ፣ አባላቶቻችን የታሰሩበትን ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ ሀገራዊ ጉዳዮች በሚመለከት አሰፈላጊውን መረጃዎች ሁሉ ከግምት ውስጥ ያስገባ መግለጫ ንቅናቄው በአጭር ጊዜ ስለሚያወጣ ነገሮችን በእርጋታና በትእግስት መጠበቅ አስፈላጊ ይመስለኛል።,

በአርቆ አሳቢነት አሁን የሚገኘው ውስብስብና በሀገሪቱ ውስጥ የተፈጠረውን በአመዛኙ እጅግ ስሜታዊና ለዜጎች ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ ድባብ ለመሻገር መጣር፣ የበኩላችንን ድርሻም መወጣት እንዳለብን ሁሉንም ወገኖች ለማሳሰብ እወዳለሁ። በቅርቡ ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አሕመድ በኦህዴድ (ኦዴፓ) ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ከዚህ በኋላ በኦሮሞ ስም መነገድ አይቻልም ብለዋል። በተመሳሳይ በአማራውም ስም፡ በደቡብ ህዝቦች ስም፣ በትግራይ ህዝብ ስም፣ በሶማሌ፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ስም መነገድ ማብቃት አለበት።በቡራዩን በአካባባዊ የተደረገው አረሜናዊ ጭፍጨፋ መሰል አረመኔያዊ ድርጊቶች እንዳይፈጽሙ ለመከላከልና አገራችን ኢትዮጵያን ለመታደግ ለሚፈልጉ ሁሉ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። ድርጊቱ የተቀነባበረው በህዝብ ስም በሚነግዱ እነዚሁ የፓለቲካ ነጋዴዎች ስለመሆኑ ብዙ ጠቋሚዎች አሉ። በአካባቢው ከተፈናቀሉት ወገኖቻችን የሰማነው እጅግ ዘግናኝ ኢ-ሰባዊና አውሬአዊ ድርጊቶች የኢትዮጵያውያን የሚያስተሳስሩ ሰበአዊና ሞራላዊ እሴቶች በለፊት 27 የዘረፋና የአፈና አመታት ምን ያህል እንደተቦረቦረ አመላካች ጭምርም ነው።

የሁሉም ማህበረሰቦች፣የሁሉም ዜጎች ደህነትና መብት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባባዎች ያልተጠበቀባት ኢትዮጵያ ትርፉ የማያባራ እሳት የሚቀሰቅስና ማንም አትራፊ የማይሆንበት ወደ ገሃነም የሚወስድ መንገድ መሆኑን መገንዘብና ማስገንዘብ እጅግ አስፈላጊ ነው። ህዝብን ከህዝብ የሚከፋፍሉ፣ የሚያጋጩ፣ ልዩነቶችን የሚያራግቡ ፣ ብሎም ለዘመናት ኢትዮጵያን እንደ አገር በጋራ የገነቡ ልዩ ልዩ ማህበረሰቦች መካከል ግጭት በመፍጠር ዛሬ ወደ ሀገራችን ገብተን የነጻነት አየር መተንፈስ የጀመርንባት የኢትዮጵያን ህልውና ከባድ አደጋ ላይ ለመጣል የሚንቀሳሱ ሃይሎችን ማጋለጥ፣ መታጋል የመንግስት ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም የፓለቲካ ሃይሎች፣ እንዲሁም የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሃላፊነት መሆኑን ተረድተን ይህን በሰላም፣በህዝቦች አብሮነት፣ እንዲሁም በለውጡ የተገኘውን ነጻነት ለመቀልበስ የሚንቀሳቀሱትን ሃይሎች የሚያቀነባብሩት ሴራ፡ የሚጋግሉት ቅራኔዎችና በየሚዲያውና ሶሻል ሚዲያዎች የሚነዙት ውዥንብሮች ሰለባ ላለመሆን ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል። ልዩ አጀንዳ ያላቸው፣ ከአለኛ አይሆንም በሚል እንዳአበደ ውሻ የሚክለፈለፉ ፣ ምንም ሀገራዊ ሃላፊነት ከማይሰማቸው ግለሰቦችና ሃሎች ጋር በስሜትና በቁጭት ተነስተው የሚደረጉ እንካ ሰላንታያ ወጥተን በሀገራዊ ሃላፊነት ስሜት፣ ትግስትና፣ ብልሀት መንቀሳቀስ ውቅቱ የግድ ይላል። አመሰግናለሁ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.