በኦሮሚያ ክልል 6700 ሰዎች ሃሰተኛ ሠነዶች ይዘው ተገኙ


ቁጥራቸው 6700 የሚሆን የኦሮሚያ ክልል የህዝብ ሰራተኞች የመንጃ ፈቃዶች እና የብቃት መማረጋገጫ ሰርቲፊኬትን (ሲኦሲ) ጨምሮ ሃሰተኛ የስራ እና የትምህርት ሠነዶችን ይዘው ተገኝተዋል። የኦሮሚያ ክልል የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀይል ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሰራተኞቹ የአመራር ስፍራን ጨምሮ በተለያዩ መደቦች ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል። እንደ ሀላፊው ገለፃ ግማሽ ሚሊዮን ከሚሆነው …