Tag: opdo

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ለከንቲባነት ኢንጂነር ታከለ ኡማን ለማዘጋጃ ቤት ሓላፊነት – ኤርሚያስ ለገሰ


ታሪካዊ መንደርደሪያ

ወቅቱ የኢትዮጵያ የሚሌኒየም አመት (2000 ዓም) መገባደጃ አካባቢ ነበር። የአዲስ አበባ ዳግም ምርጫ ተካሂዶ የከተማው ከንቲባ፣ ካቢኔ ፣ የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚና ካቤኔዎች በኢህአዴግ ቢሮ የምንመድብበት ነበር። ስራው በፍጥነት መሰራት ስለነበረበት አቢይ ኮሚቴ እና ንዑስ ኮሚቴ ተደራጅቶ የሚፈፀምበት ነበር።

አቢይ ኮሚቴው የሚመራው በአቶ በረከት ሲሆን ተመልማዬችን ፕሮፓዛል ይዘን የምንመጣው የኮሚቴው አባላት አቶ አርከበ እቁባይ፣ ህላዌ ዬሴፍ፣ ካሚል አህመድ፣ ፀጋዬ ኃ/ማርያም፣ ፍሬህይወት አያሌው፣ ይሳቅ አበራ(ቆሪጥ) እና እኔ ነበርን።

እናም አቢይ ኮሚቴው በበረከት ቢሮ ተቀምጠን ለመዲናይቱ ከንቲባ፣ ምክትል ከንቲባና ካቢኔ የሚሆኑትን መምረጥ ጀመርን። ለአዲስ አበባ ምክርቤት ከተወዳደሩት አባላት ውስጥ ለከንቲባነት እጩ ሆነው የቀረቡት አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ ወይዘሮ አስቴር ማሞ እና አቶ መላኩ ፈንታ ነበሩ።

በመጀመሪያው ዙር በረከት በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ ቅሬታ በማንሳቱና ብአዴን ባለበት እንዲቀጥል ትፈልጋለች በማለቱ መላኩ ፈንታ ውድቅ ተደረገ።በክርክሩ ወቅትም ሳይነሳ ቀረ። እናም የተቀሩት ሁለቱ ኦህዴዶች ሆኑ። ኩማ ደመቅሳና አስቴር ማሞ። አሁንም በረከት የድርጅቱ (የባለቤቱ ወይዘሮ አዜብ በተለይ) ፍላጐት ወይዘሮ አስቴር ማሞ ከንቲባ እንድትሆን ነው በማለት እንቅጩን ነገረን። ሁላችንም ተቃወምን። በተለይ አርከበ በንዴት እየተንጨረጨረ ቅሬታውን አቀረበ። ይህም ሆኖ የድርጅቱ እና የሚስታቸው ውሳኔ በመሆኑ የሚቀለበስ ነገር እንደሌለ ተነገረን። የመጨረሻ ቀጠሮ ለሚቀጥለው ሳምንት አስረን ተለያየን።

የቀጠሮው ቀን እስኪደርስ የነበሩት ቀናት የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ለነበርን ሰዎች ከፍተኛ ሴራ ከጠነሰስንበት ጊዜያቶች የላቀውን የሚይዝበት ነበር።

በአንድ በኩል በካድሬዎች አማካኝነት የአዲስ አበባ ሕዝብ በወቅቱ የመከላከያ ሚኒስትር የነበረው ኩማ ደመቅሳ ከንቲባ እንዲሆን መፈለጉት አሰራጨን። ከሰላሳ ሺህ በላይ መጠይቆችን በማዘጋጀትና በመሙላት 75 በመቶ ኩማን፣ 15 በመቶ መላኩ ፈንታንና 3 በመቶ ወይዘሮ አስቴርን ከንቲባ ሆነው ማየት እንደሚፈልግ አመላከትን።

በሌላ በኩል ተነባቢ ለነበሩ የግል ጋዜጦች ቀጣዩ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ እንደሚሆን የውስጥ መረጃ በመስጠት ጋዜጦቹን በኩማ ፎቶ አደመቅናቸው። አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ድርጅቱ ሃሳቡን ቀይሮ ኩማ ደመቅሳን ከንቲባ ለመመደብ ተገደደ።

ከሁሉም አስቂኙ ነገር አቶ ኩማ ከንቲባ እንደሚሆን የተነገረው ምክርቤቱ ሊጠራ በዋዜማው ስለነበር ድንግርግሩ ወጥቶ ነበር። በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ያነበበው የአስተዳደሩ የአመቱ መሪ እቅድ የተመለከተው የእለቱ እለት ነበር። በአካልና በስም የማያውቃቸውን የካቢኔ አባላት ጽብፃብ ኮስተር ብሎ ሲያነብ ራሱ ያዘጋጃቸው ይመስል ነበር። ኩማ ደመቅሳ እንዲህ ነበር።

***

ከላይ የተጠቀሰውን ታሪክ ወደ ኃላ ሄጄ የማነሳበት የተወሰኑ ምክንያቶች አሉኝ። እስከ አሁን ድረስ የአዲስ አበባ ከንቲባነት የሚገኘው በህዝብ ምርጫ ሳይሆን በፓርቲ ምደባ እና ክፍፍል ነው። ከንቲባውም ተጠሪነቱ ለፓርቲውና ለመደበው ግለሰብ ነው። ይሄ ባልተለወጠበት ሁኔታ የፓርቲ ምደባ ላይ መሻኮትና እርስ በራስ መደባደብ የለውጥ ሂደቱን እንዳይፋጠን ከማድረግ ውጪ የሚፈይደው ነገር የለም። ከዚህ አንፃር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ “ በሁሉም መራጭ ህዝብ ያልተመረጠ ሰው ፕሬዝዳንት (“ከንቲባ”) ነኝ ሊል እንደምን ይቻለዋል?” በማለት የተናገሩትን ማስታወስ ይበጃል።

እናም ጠቅላይ ሚኒስትሩን መጨቅጨቅ ያለብን በቀጣዩ ምርጫ የአዲስ አበባ ከንቲባ የሚሆነው ከ1 ሚሊዬን የአዲሳባ መራጭ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዬን በላይ የመረጠው ብቻ እንዲሆን ቻርተሩን እንዲያሻሽሉልን ነው። የአዲስ አበባ አጠቃላይ መራጭ ህዝብ ወደ አንድ ሚሊዬን ይጠጋል የሚል ታሳቢ ወስጄ ነው። እናም ይሄ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ ፍፁም ፍላጐት ከመሆኑም በላይ የመዲናይቱን የፓለቲካ ሽኩቻና የዘር መጓተት ተቋማዊ በሆነ መንገድ የሚፈታ ይሆናል። አንድ ድምፅ ለአንድ ሰው የሚል መርሆ ያለው የፕሮፌሰር መረራ ፓርቲም በውሳኔው ደስተኛ እንደሚሆን አልጠራጠርም። መቼም በዚህ የውሳኔ ሃሳብ የሚከፋ ሰው ካለ ወይ ዲሞክራሲ አልገባውም አሊያም ለአዲስ አበባ ህዝብ ክብር የለውም። አልፎ ከሄደም የአዲስ አበባን ህዝብ ይጠላል። ድፍን የአዲስ አበባ ህዝብ በግሉ የምርጫ ውሳኔ ከንቲባውን መርጦ ሲደሰት የሚከፋው ከሆነ ቦታው አማኑኤል መሆን አለበት።

ከዚህ በተጨማሪም ከግማሽ ሚሊዬን በላይ የሚሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ የመረጠው ከንቲባም ደረቱን ነፍቶ “ ሕዝብ የመረጠኝ ነኝ!” ማለት ይችላል።ትችላለች።

***

ወይዘሮ ዳግማዊ ሞገስ የአዲስ አበባ ከንቲባ

ከላይ የተቀመጠው የቻርተር ማሻሻያ የውሳኔ ሃሳብ ወደ ተግባር እስኪለወጥ ድረስ የሚመደበው ከንቲባ በህዝብ ያልተመረጠ በመሆኑ ራሱን እንደ ሽግግር ከንቲባ መውሰድ ይኖርበ(ባ)ታል። ይሄ(ቺ) ከንቲባ ጊዜያዊ እንደመሆኑ(ኗ) መጠን በተቻለ መጠን የህዝቡን ውስን ፍላጐቶች ቢያ(ታ)ሟላ ጥሩ ይሆናል።

በመሆኑም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨዋውን ፣ ያላሳፈሮትን፣ በችግር ጊዜ ከጐኖ ቆሞ ያኮራዎትን የአዲስ አበባ ነዋሪ ፍላጐት ለማሟላት ወይዘሮ ዳግማዊ ሞገስን በከንቲባነት ፣ ኢንጂነር ታከለ ኡማንን ደግሞ በማዘጋጃ ቤት ሓላፊነት እንዲመርጡ ፍቃድሆ ይሁን። የዛሬ ውሳኔዎትን መልሰው አጢነውት ሽግሽጉን በአስቸኳይ ይፈፁሙ። አለበለዚያም ምክንያቶን ያስረዱ።

ወይዘሮ ዳግማዊ ሞገስ የአስተዳደሩ ከንቲባ እንድትሆን የማቀርባቸው ምክንያቶች ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው።

1. ዳግማዊት አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች ናት። የኮልፌ ቀራንዬ ልጅ የሆነችው ዳግማዊት አዲስ አበባን ከግር እስከ ራሷ ታውቃታለች። የህዝቡን ማንነት እና ስነ ልቦና ጠንቅቃ ትገነዘባለች።

2. ዳግማዊት ወደ አዲስ አበባ መስተዳድር ስናመጣት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር ነበረች። በዛን ሰአት እድሜዋ ከ21 እስከ 23 አመት ውስጥ እንደነበር አስታውሳለሁ። በአሁን ሰአትም እድሜዋ ከ33 የሚበልጥ አይመስለኝም። ዳግማዊት በዩንቨርስቲው መምህር ሆና ልትቀር የቻለችው በትምህርቷ በጣም ጐበዝና የከፍተኛ ማዕረግ ምሩቅ ስለነበረች ነው። የዩንቨርስቲ መምህርነቷን ለቃ ስትመጣ በፍፁም ህዝብ የማገልገል ፍላጐት ሰንቃ የመጣች ሲሆን በዝዋይ አላጌ በነበረው የሁለት ወር ስልጠናም በቅርበት ማረጋገጥ የቻልኩት ሁለንተናዊ እይታዋን ነው።

በነገራችን ላይ በአንድ ወቅት ዩንቨርስቲውን ለቃ መምጣቷ ቅር እንደሚያሰኘኝ ሳልደብቅ ነግሬያታለሁ። ያለምንም ጥርጥር በዩንቨርስቲ ቆይታዋ ቢራዘም ኖሮ ሶስተኛ ዲግሪዋን ይዛ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የምትወዳደርበት አቅም ታዳብር ነበር።

3. ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የአዲስ አበባ ምክርቤትና የካቢኔው አባል ስለሆነች ክቡርነትዎ እሷን ጊዜያዊ ከንቲባ ለማድረግ ህገ መንግስትና ቻርተር መጣስ አይጠበቅቦትም። በአዲስ አበባ ታሪክም የሚያስቀምጡት ጥቁር ጠባሳ ሳይሆን የተስፋ ብርሃን ይሆናል። ወጣቷ ወይዘሮ ከክፍለ ከተማ ጀምሮ የመዲናይቱን ቢሮክራሲና አሰራር የተመለከቱት ስለሆነ የእሮሶ ድጋፍ ከተጨመረበት በአጭር ጊዜ የለውጥ ሃዋርያው መሪ ትሆናለች።

4. እስከማውቀው ድረስ ወይዘሮ ዳግማዊት ሌብነት እና ዝርፊያን የምትጠየፍ እንስት ናት። ሙሉ ፍላጐቷ ህዝብ የማገልገል ስለሆነ እንደዚህ አይነት ራስን ዝቅ የሚያደርግ ወራዳ ስራ ውስጥ እጇን የምትነክር አይመስለኝም። እርሶም በአሁን ሰአት የምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሰጧት ይሄን ተመልክተው ይመስለኛል።

5. ወጣት ዳግማዊት የጠንካራ ሴት ተምሳሌት ናት። ይህቺን አርአያ የምትሆን ጠንካራ ሴት እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በከንቲባነት መሾም ትልቅ ክብር ነው። የሴትየዋ ስም በታሪክ ውስጥ ሲነሳ የእርሶም ስም አብሮ ይነሳል። እስቲ ይታዮት ከእለታት አንዲቷ ቀን የማዘጋጃ ቤት የምክር ቤት አዳራሽ ገብተው የተሰቀሉትን ከመጀመሪያ እስከ ዛሬ የነበሩ ከንቲባዎች ውስጥ የአንዲት ሴት ፎቶ ብቻ ተሰቅሎ ሲመለከቱ የሚሰማዎት ስሜት? ያውም በእርሶ ዘመን። የዛኔ እኛም “ታሪክ በታሪክ ሰሪዎቹ ተሰራ!” ብለን ለመፃፍ እንታደላለን። እናም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይረፍድብዎ ታሪክ ይስሩ።

ኢንጂነር ታከለ ኡማን የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሓላፊ

ኢንጂነር ታከለ ኡማንን የማዘጋጃ ቤት ኃላፊ እንዲሆን የምፈልግበት ምክንያት በአጭሩ ልግለፅ። እንደገባኝ ከሆነ ኢንጂነር ታከለን የፈለጉበት ምክንያት በዋናነት የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጅ በመሆኑ ሳይሆን የእርሶ የለውጥ ሐዋርያ ቡድን ውስጥ የታቀፈ ሰው ስለሆነ ይመስለኛል። ባይሆን ኖሮ የድርጅቶ ፕሮግራም የተገለፀበትን ህገ መንግስት እና ቻርተር እስከ መጣስ የሚያዘልቆት አይመስለኝም። እንደዚህ ከሆነ ዘንዳ ህግ ሳይጥሱ ይሄን የእርሶ የለውጥ ሐዋርያ ቁልፍ ቦታ ላይ መመደብ የሚቻልበት እድል አለ።

በእኔ እምነት በአዲስ አበባ የስልጣን እርከን ውስጥ ሶስት ቁልፍ ቦታዎች አሉ። ከንቲባ፣ የማዘጋጃ ቤት ሐላፊ እና የፓርቲ ጽህፈት ቤት ሐላፊ። እነዚህን ሶስት ቦታዎች በእርሶ የለውጥ ሐዋርያ ቡድን መቆጣጠር ከቻሉ ሌላው እዳው ገብስ ነው። ዛሬ የማዘጋጃ ቤቱ እና የፓርቲው ጽህፈት ቤት የተያዘው የቀን ጅቦች በሆኑት የህውሓት ካድሬዎች በሆኑት ሓይሌ ፍስሃና ተወልደ ነው። እነዚህን አደገኛ ሰዎች ወደ መጡበት ማሰናበት ጊዜ የሚሰጠው አይደለም። ለበለጠ መረጃ አጠገቦት ቺፍ ኦፍ ስታፍ ያደረጉትና የቀድሞ የአዲስ አበባ ጥቃቅን ሐላፊ የነበረውን ፍፁም አረጋ መጠየቅ ይችላሉ።

ግልባጭ: ለፍፁም አረጋ (ቺፍ ኦፍ ስታፍ)

ለማ መገርሳ( ፕሬዝዳንት)

Advertisements

Stop Confusing the Ethiopian Flag with the Insignias and Emblems of Ethiopia’s Changing Regimes [by Birihanemeskel Abebe Segni]


Let’s stop confusing the Ethiopian flag with the Insignia and Emblems of Ethiopia’s changing regimes. Each Ethiopian regimes from Emperor Menelik to Emperor Haile Selassie and from the Derg Regime to the TPLF regime adopted their own insignia and emblems and inscribed it on the Ethiopian flag. Those insignias and emblems were changing as the regimes change.

Continue reading “Stop Confusing the Ethiopian Flag with the Insignias and Emblems of Ethiopia’s Changing Regimes [by Birihanemeskel Abebe Segni]”

በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የሃይል አሰላለፍ – ፋሲል የኔዓለም


ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው ከተመረጡ ወዲህ በሁሉም ወገን ያለው ግራ መጋባት እንደቀጠለ ነው። Continue reading “በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የሃይል አሰላለፍ – ፋሲል የኔዓለም”

በተጠናቀቀው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በአባይ ጸሃዬ የተማራው ህወሃት ከኦህዴድ ባለስልጣናት ጋር ጸብ ቀረሽ ክርክር ማድረጉ ታወቀ – ኢሳት


የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ለሳምንት በተደገረው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ህወሃት በአቶ አባይ ጸሃዬ ዋና ተከራካሪነት ተወክሏል። ከአቶ አባይ ጀርባ አቶ ስብሃት ነጋና አቶ በረከት ስምዖን ተሰልፈው በኦህዴድ ላይ ከፍተኛ ዘመቻ አድርገዋል። ኦህዴድ በአቶ ለማ መገርሳ ዋና ተከራካሪነት ሲቀርብ፣ ዶ/ር አብይ አህመድም ከአቶ ለማ ጀርባ ሆነው ክርክራቸውን አድርገዋል። Continue reading “በተጠናቀቀው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በአባይ ጸሃዬ የተማራው ህወሃት ከኦህዴድ ባለስልጣናት ጋር ጸብ ቀረሽ ክርክር ማድረጉ ታወቀ – ኢሳት”

ሰአቱ ደርሶ ይሆን? (ዮሐንስ መኮንን)


የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ከ ስምንት ወራት በፊት ዓለማችንን በርዕዮተ ዓለም ለሁለት ስለሰነጠቃት የቀድሞዋ ታላቋ ሶቭየት ኅብረት ገናና መሪ ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ሲናገሩ ”በሀገራችን ቦንብ አጥምዶ ያለፈ መሪ” ሲሉ ባልተለመደ ሁኔታ ወቅሰውታል፡፡ ፑቲን ምክንያታቸውን ሲያስረዱ ”ሌኒን የተከለብን በዘር ላይ የተመሠረተ የክልሎች አወቃቀር ሀገራችንን ሰላም የራቃት ሉዓላዊነቷም አደጋ ላይ የወደቀ አድርጓታል፡፡” ሲሉ ወቅሰውታል፡፡ በክሬሚያ እና በሌሎችም የሩሲያ ግዛቶች የሚታየው ምስቅልቅል መንስኤው ሌኒን ያጠመደው ወቅቱን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ (Time bomb) ነው ሲሉ አብራርተው ነበር፡፡

የኮሚኒስቶቹ የብሔር ፈንጂ የተቀበረው በሩሲያ ብቻ አይደለም፡፡ የሌኒንን እኩይ ምክር የሰሙ እኛን የመሰሉ ሀገራት ጭምር እንጂ፡፡ በየካቲት ወር 1968 ዓም በእጅ ተጽፎ የተሰራጨው የመሪዎቻችን ”መግለጫ” የተባለው ጽሑፍ በገጽ 8 ላይ ”የኅብረተሰብ መደብ መከፋፈል ለማጥፋት የተጨቋኙ መደብ አምባገነንነት እንደሚያስፈልግ ሁሉ የማይቀረው የብሔሮች መዋሀድ ሊገኝ የሚችለው መሸጋገሪያ በሆነው የብሔሮች ነጻነት ማለት የብሔሮች መገንጠል መብት ሙሉ በሙሉ መኖር ሲችል ብቻ ነው” የሚለውን የሌኒንን ርዕዮት በመጥቀስ የብሔሮችን ግንኙነት ለመወሰን አብነት በመውሰድ ይተነትናል፡፡

ባለፉት 25 ዓመታትም በሀገራችን የተዘራው የልዩነት ዘር እነሆ ፍሬ ይዞ ”የምሥራቹን” በአንዳንድ የሀገራችን አከባቢዎች እያየን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና ኦሮሚያ የተፈናቀሉትን ወገኖቻችን ቁጥር ስናይ፣ ሰሞኑን ደግሞ በአንዳንድ ቦታዎች ዘር የለየ ዜጎችን ለሞት ለንብረት ቃጠሎና ለስደት የዳረገ ክስተት (በኦክቶበር 21-2017 ቢቢሲ የትግርኛው ዝግጅት እንደዘገበው) ስናስተውል የተቀበረው ወቅት ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ (Time bomb) ጊዜው ደርሶ ይሆን? እያልን እንሠጋለን፡፡ እንሳቀቃለን፡፡

ፑቲን ራሳቸው የኮምኒስት ሀሳብ አቀንቃኝ እና የኬጂቢ ሰላይ የነበሩ ሲሆን ”ያኔ የሠራነው ስህተት ነው፡፡ ያሰብናት ሩሲያም በምድር ላይ አልነበረችም” በማለት በጸጸት ተናዝዘዋል፡፡ ማንኛውም ሰው በወጣትነቱ አብዮተኛ፣ በአማካይ እድሜው ሚዛናዊ፣ በሽምግልናው ደግሞ መንፈሳዊ ዝንባሌ አለውና የፑቲን ጸጸት ተገቢ እና የሚጠበቅ ነው፡፡ ጥያቄው በሌኒን የብሔር ተቃርኖ ፍልስፍና የተጠመቁት የኛዎቹ የዛኔዎቹ አብዮተኞች የአሁኖቹ አረጋውያን መቼ ነው የሚጸጸቱት? የሚል ነው፡፡ ያኔ ያሰባቧት ኢትዮጵያ በምድር ላይ የለችምና! የተዘራው ዘር መራራ ፍሬ ሲያፈራ በስተርጅና እየታዘቡት ነው፡፡ ”ያኔ በወጣትነታችን ያሰብነው ስህተት ነበር፡፡ ሁላችንም በመደማመጥ የምንጓዝበት አዲስ መንገድ ያስፈልገናል” ብሎ ለመታረም ስንት ሰው መሞት፣ ምን ያህል ህዝብ መፈናቀል፣ ምን ያህልስ ንብረት መውደም ይኖርበት ይሆን?

መፍትሔው አንድ ነው፡፡ ሁላችንንም አሸናፊ የሚያደርግ እና መደሰላም መስክ የሚያሻግረንን ድልድይ ለመገንባት እጅ ለእጅ ለመያያዝ ምናልባትም የቀሩን ጊዜያት ብዙ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ አሁን እየታዘብነው እንዳለነው ከሆነ ፈንጂው በማንኛውም ሰአት ቢፈነዳ ከመሀከላችን ለወሬ ነጋሪ የሚተርፍ መኖሩን መተንበይ አይቻልም፡፡

የዘረኛው ህወሐት የምስረታ ሰነድ በቁጥር አንድ ጠላትነት ያስቀመጠው ህዝብ (ECADFORUM)


ህወሐት በትግል ፕሮግራሙ የአማራን ያክል የሚጠላው ሌላ ህዝብም ሆነ አካል እንደሌለ በግልጽ ያስቀመጠ ድርጅት ነው። የአማራ ህዝብ መሬት እያረሰ የሚኖር ደሀ ህዝብ ቢሆንም በህወሐት የምስረታ ሰነዶች እንደ ገዥ ብሄር ተፈርጆአል። አስገራሚው ነገር አማራ ንጉሱንም ሆነ ደርግን በማስወገድ ትግል ከሌሎች ህዝቦች እኩል ድርሻ የነበረው ህዝብ ነው። እንደ ህዝብ በህወሐት የሚጠላው በተጨበጠ ምክንያት አይደለም። ህወሐት የአማራን በሌሎች እንዲጠላ ካደረገባቸው የተደራጁ ስብከቶች በተጨማሪ የብሄረሰቡን ማንነት የሚያዳክምባቸው ልዩ ልዩ እርምጃዎችንም ወስዶአል።


Get a Free Gift with any purchase.

አንዱ ሴቶች ፍላጎታቸው ሳይጠየቅ የረጅም ግዜ የወሊድ መከላከያ መርፌ እንዲወጉ ማድረጉ ነው። በዚህም እኤአ 2007 የህዝብ ቆጠራ የህዝብ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በ3 ሚሊዮን የቀነሰ ብቸኛ ህዝብ ሆኖአል። ሌላው በትግራይ ክልል የልዩ ወረዳ አስተዳደር ክብር የሚገባቸው ልዩ ልዩ ብሄረሰቦች እያሉ ህወሐት አማራ ክልል መጥቶ የልዩ ዞን ፍላጎት ቀስቀሰሽና አስፈጻሚ መሆኑም ከዚሁ አማራን ለማዳከም ካለው ጽኑ ፍላጎት ጋር ይያያዛል። የአማራን ክልል መሬት በጉልበት ወደራሱ የማካለል ስራም ሌላው ተግባሩ ነው። እራሳቸውን በአማራነት የሚገልጹ ሰዎችን በግፊት ወደ ትግሬነት የመቀየር ስራም ሰርቶአል። ህወሐት በፕሮግራሙ ውስጥ አማራን ግንባር ቀደም ጠላቴ ነው ብሎ ከመጻፍ ጀምሮ በተከታታይ በዚህ ህዝብ ላይ እየፈጸማቸው ያሉ ግፎች መነሻቸው ምንድን ነው?


የመጀመሪያው መሰረታዊ ምክንያት ህወሐት ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ፈጽሞ ማየት አለመፈለጉ ነው። ይህ ጥላቻ ምንጩ የወራሪው ኢጣልያ አገልጋይ ከነበሩ ጥቂት ባንዳ የትግራይ ልጆች ነው። እነዚህ በቀድሞው የህወሐት አባል በአቶ ገብረመድን አጠራር ሻምቡሽ እየተባሉ የሚጠሩት የትግራይ ባንዳዎች በልጆቻቸው በኩል ስብከቱን በማጉላት በአሁኑ ወቅት ብዙ ተከታይ አግኝተዋል ። የአማራ ህዝብ ደግሞ ፖለቲከኛ ሆነ ደሀ ገበሬ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሀገሪቷን ከወራሪ ሲከላከል የቆየ ህዝብ ነበር።

40% OFF EVERYTHING* ! End date November 1st, 2017.

በዚህም ቂም ተይዞበታል። ብዙዎች የዋሆች ህወሐት ኢትዮጲያዊ መባል ካልፈለገ ለምን ታዲያ ሁሉን አድራጊ በሆነበት በአሁን ወቅት መገንጠልን አይፈጽመውም የሚል ጥያቄ ይጠይቃሉ። መልሱ የትግራይ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የስነልቦና የበላይነቱ እስካልተነካበት የመገንጠል ፍላጎቱን ገሀድ አያወጣም የሚል ይሆናል። አዎ እንደ ነብር ደምህን እየመጠጠ ይቆያል። ደምህ ካለቀ ወይም አሻፈረኝ ካልክ ግን ያኔ ይተገብረዋል።

Create your own Yvesrocherusa.com or yvesrocher.ca link

ሁለተኛው ምክንያት የተለመደው የከፋፍለህ ግዛ ባህሪው ነው። ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን ኣስፈራርቶ ለመግዛት የሚፈሩት ጠላት ሊፈጥርላቸው ይገባል። ለዚህም አማራን አስቀምጦላቸዋል። በሁለተኛነትም ከአማራ ህዝብ ጋር ህብረት እንዳይፈጥሩ ማድረጊያ ስልቱም ነው። ይህ ስልቱም ከጠበቀው በላይ ሰርቶለታል። በዚህም የአማራ ህዝብ ለትውልዶች ከኖረባቸው አካባቢዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶች ተፈጽሞበታል። በኦሮሚያ፣ ደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የተፈጸሙትን ግድያዎችና ማፈናቀል መጥቀስ ይቻላል።

የአለም ህዝቦች መልቲ ካልራሊዝምን እንደ ሀብት በሚቆጥሩበት በዚህ የስልጣኔ ዘመን አባቶቹ የጣልያን ሻምቡሽ ሆነው የተነገራቸው ስብከት ላይ ተቸንክሮ የቆመውን ህወሐት በተግባር በቃ ልንለው ይገባል። አለበለዚያ ግን የሰሞኑ የአለም ባንክ ይፋ ያወጣው የኢትዮጵያ ክልሎች የመንገድ ግንባታ ግስጋሴ የ 10 ዓመት ሪፖርት በግልጽ እንዳስቀመጠው (ትግራይ ክልል አንደኛ እንዲሁም አማራ መጨረሻ) ህወሀት የአማራንም ሆነ ሌሎች ህዝቦችን ደም መምጠጡን ይቀጥላል።

በያሬድ አውግቸው

ECADFORUM